Get Mystery Box with random crypto!

ንሥር እንግዳ ነሃሴ 27/2014 በታሪክ ከማልዘናጋቸው ነገሮች አንዱ የአማራው ልዩ ሃይል ተግባ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

ንሥር እንግዳ
ነሃሴ 27/2014

በታሪክ ከማልዘናጋቸው ነገሮች አንዱ የአማራው ልዩ ሃይል ተግባር ነው።

"መቶ አለቃ ሺብሩ ጌትነት"

እውነት ነው "የአማራ ልዩ ሃይል" ተዋጊ ነው።
የአርቢት፣የደብረዘቢጥ እና የጋሺና ምሺጎችም ይመሰክራሉ። ልዮ ሃይሉ ከብዙ ተቋሞች የተወጣጣ የአማራ ህዝብ መከታ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን ነው።


እውነት ነው የአማራ ህዝብ የምንጊዜም ጠበቃ ነው።
ጠላትን በየአቅጣጫው እየደመሰሰ የማይዝል ክንዱን እየቀመሰ ይገኛል። የአማራ ልዩ ሃይል ተጠናክሮ መቋቋም ከጀመረበት 2011 ዓም ጀምሮ ያለ ዕረፍት እየተዋጋ ያለ ሃይል ነው። በዚህም በሁሉም የአማራ አካባቢዎች ያለ ዕረፍት የተዋጋ ሰራዊት ነው።

ሰራዊቱ ከቅማንት ፀንፈኛ ቡድን፣ከትህነግ፣ ከኦነግ ሸኔ፣ከቤሻንጉል አማፂ ጋር ከሰሜን እስከ ደቡብ ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ተዋግቶ ጠላቶቹን አሳፍሯል። በሁሉም የአማራ ምድር ላይ ደሙን አፍስሷል አጥንቱንም ከስክሷል።

ስለሆነም ወድ ወገኔ ሆይ ከአማራ ልዩ ሃይል ጎን ልንቆም ይገባል።
እውነት ለመናገር በትንሺ ክፍያ ውድ ህይወቱን እያጣ ያለውን ልዩ ሃይላችንን አይዟችሁ ልንላቸው ይገባል።

የአማራ ልዩ ሃይል ጀግና ሰራዊት መሆኑንም እንድህ ያሉ መስመራዊ መኮነኖችም እየመሰከሩለት ነው። ስለዚህ እየተከፈለልን ላለው ነገር ሁላችንም ልናመሰግነውና ልናበረታታው ያስፈልጋል።
ክብርም ልንሰጣቸው ይገባል። የአማራው የመንግስት አስተዳደሮችም ልዩ ሃይላችንን የመንከባከብ ግደታ አለባችሁ።

ስለሆነም ክብር ለልዩ ሃይላችን እንላለን።

ንሥር እንግዳ
ነሃሴ 27/2014

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።

ንሥር ብሮድካስ በተለያዮ የራያ አውደውጊያወች ከሚገኙ ነዋሪወችና ፋኖወች ጋር ያደረገው ቆይታ
ንሥር ብሮድካስ በራያ፤ በመርሳ፤ ኮምቦልቻ፤ ወልድያና በሌሎችም አውደ ውጊያወች ዘገባወችን ያቀርባል