Get Mystery Box with random crypto!

111 ህገወጥ የዲጂታል ሚዲያዎች ኢትዮጵያን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሰሩ በነበር ሚዲያዎች ላይ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

111 ህገወጥ የዲጂታል ሚዲያዎች ኢትዮጵያን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሰሩ በነበር ሚዲያዎች ላይ ክስ ተመስርቷል :- የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

ንሥር ብሮድካስት
ነሐሴ 25/2014

በተጠናቀቀው 2014 በጀት ዓመት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ኢትዮጵያን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሰሩ በነበሩና በመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ህጋዊ እውቅና በሌላቸው 111 የዲጂታል ሚዲያዎች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮሚሽኑ የታክቲክ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዋና መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተደራጁና የሽብር ወንጀሎች፣ በሙስና፣ በፋይናንስና ንግድ ነክ፣ በታክስና ጉሙሩክ ወንጀሎች ላይ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ምርመራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

በዚህም መሰረት 2 ሺህ 668 ጥቆማዎችን በመቀበል 1 ሺህ 438 መዝገቦችን መርምሮ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መላካቸውንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ ሀገሪቱን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሰሩ በነበሩና ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ስያሜ በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ በነበሩ አካላት ላይ ክስ መመስረቱን ተናግረዋል፡፡

እነኚህ አካላት ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም በምርመራ መረጋገጡን ነው ያብራሩት።

መረጃ ተጣርቶባቸው ክስ የተመሰረተባቸው 111 የሚሆኑት የዲጂታል ሚዲያዎች በመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ህጋዊ እውቅና እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜም የእነኚህ ህገወጥ የዲጂታል ሚዲያ ባለቤቶች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑንም ጠቅሰው በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉት ሚዲያወች ዝርዝር ግን ግልፅ አልተደረጉም:: ዘገባው የዋልታ ነው::

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram: https://t.me/nisirbroadcasting
Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1