Get Mystery Box with random crypto!

ከንሥር እንግዳ ነሐሴ 24/2014 ****************** አማራን ከታሪክ ከፍታው በማውረድ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

ከንሥር እንግዳ
ነሐሴ 24/2014
******************

አማራን ከታሪክ ከፍታው በማውረድ ሂደት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው አሻጥረኛው የብአደን አመራር ነው።

የህዝባችን መራራ ተጋድሎ ውጤት አድስ መሪዎችን መውለዱ አይቀሬ ነው።

ጀግናው የአማራ ህዝብ ራሱን እንደ ንስር የሚያድስበት ጊዜው አሁን ነው።

ጠንካራው ህዝብ በሰነፍ መሪዎች እየተመራ የመከራ ዘመን ላይ ይገኛል።

ህዝባችንን እጅግ አብዝቶ የመናቅ ፓለቲካውስ ማብቂያ መቸ ይሆን??

የአማራን ህዝብ ተገማች እና አሳልፎ የመስጠት ፓለቲካስ ምንጩ ምን ይሆን??

አማራ በታሪኩ ከብአደን በላይ ጠላት የለውም።
የአማራ ጠላቶች አማራን #ተገማች ያደረጉ ከሃድ መሪዎቹ ናቸው።

የሚመሩትን ህዝብ የናቁ፣የመዘበሩ እና ለቁስ ፍላጎት ማሙያ ያደረጉትን ጥቅመኛ መሪዎች ሁሉ ለፍርድ ያላቀረበ ህዝብ አሁን በየአቅጣጫው የሚደርስበትን ዘር መጥፋት አምኖ በመቀበል ከዘር አጥፊዎች አንዱ #ብአዴን መሆኑን ያለምንም ማቅማማት መረዳት አለበት።

የአማራን ህዝብ አቅሙን፣ጉልበቱንና ህልውናውን ያጣው በራሱ የአብራኩ ክፋዮች መሆኑን መላው የአማራ ህዝብ ሊያምን ይገባል።

የአማራን ጀግኖች እየበሉ እና ድመት ሆነው እያሳደኑ ያሉ አካላት እነማን እንደሆኑ በግልፅ እየታወቀ ነባር ጠላትን ቁጭ አድርጎ ሌላ መስዋአትነት መክፈል ተቀባይነት የለውም።

ነባር የብአደን ቅጥረኛ ዛሬም በህዝባችን ላይ ተጨማሪ ክህደት መፈፀማቸው አይረሳም።

ትላንት የአማራን ህዝብ ለሃጫም እና በጥቁር ክላሺ ስም ያለስሙ ስም የሰጡት ሁሉ እውነት ከአማራ ወገን ናቸውን??

የአማራ ብልፅግና ተወካይ በቅርብ ጊዜ የተናገሩትን ክህደት አንረሳውም።
መላውን አማራ ተሳድቦ እንደትስ የአማራ ህዝብ መሪ ሊሆን ይገባዋል??

ህዝብን በአደባባይ የተሳደበ እና በህወሓት እንድንወረር ምክንያት የሆነ በህዝብ ላይ አሻጥር የሰራ መሪ እንደትስ ጠላትን ሊመክት ይችላል??

ስለሆነም የአማራ ህዝብ መደበኛ ጠላቶችህን እወቅ!!
ከትህነግ በላይ እጅና እግርህን በመዋቅር ያሰረህን ሃይል ታገል።

ግርማ የሺጥላ እና ካቢኔው የአማራ ህዝብ ተገማች እና ተወራሪ እንዲሆን በአደባባይ መስራታቸውን ልንዘነጋ አይገባም።

የአማራ ህዝብ ጀግኖችን እያስጨረሰ ዘራፊ እና መሬት ወራሪዎችን ከጠላቱ በላይ ሊታገላቸው ይገባል።

የአማራን ህዝብ አንድነቱንና ህልውናውን አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደረጉ ጥቂት ባለሀብቶችና ጥቅመኛ ካድሬዎች መሆናቸውን እወቅ።

የህዝባችን አይነኬ በሺታዎች ሆነው የቆዩት የስርዓቱ አገልጋዮችና ትግልን ለጥቅመኝነት የዋሉ ባለስልጣኖች ናቸው።

ስለሆነም ህዝባችን ከተለመደው ድብታ ውስጥ በመውጣት አሳልፎ የሰጠህንና በንቀት ተቦጅኖ ልምራህ የሚልህ ጋጠ ወጥ አመራር ላይ አተኩር።

ጠላትንና ወዳጅን መለየት ለትግሉ መዳረሻ መፍትሔም ይሆናል።
አንድ ቦታ ላይ ተቸንክሮ የሚበዘብዝህን ሳታስወግድ ሌላ ጠላት ፍለጋ መሄድ ትርፉ ድካም ብቻ ነው።

ህዝቤ ሆይ ለምን ብለህ ጠይቅ???

ከንሥር እንግዳ