Get Mystery Box with random crypto!

በጋሞ ዞን ከምባ ወረዳ ሙሉ በሙሉ የጋሞኛ ሌሎች የአከባቢ ቋንቋ ተናጋሪ የመጽሐፍ መምህራን የሆኑ | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

በጋሞ ዞን ከምባ ወረዳ ሙሉ በሙሉ የጋሞኛ ሌሎች የአከባቢ ቋንቋ ተናጋሪ የመጽሐፍ መምህራን የሆኑ ሊቃውንትን ለማፍራት ታስቦ ከ1.4 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ ያለው ጉባኤ ቤት
***

ሙሉ በሙሉ በአንድ ወንድማችን በጎ አድራጊነት በጻድቁ አባታችን አቡነ እጩጌ ዮሐንስ መታሰቢያ ስያሜነት ከ1.4 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ ያለው የከምባ ወረዳ አብነት ትምህርት ቤት በቅርብ ወራት ተመርቆ ደቀመዛሙርታትን ይቀበላል።

ጉባኤ ቤቱ በዋናነት የመጽሐፍ ጉባኤ የሚዘረጋ ሲሆን ሙሉ በሙሉ የጋሞኛ እና በጋሞ ዞን አጎራባች አከባቢዎች ያሉ የአከባቢ ቋንቋ ተናጋሪ የመጽሐፍ ሊቃንትን ለማፍራት ታስቦ የተቋቋመ በሀገረስብከቱ የመጀመርያው የመጽሐፍ ጉባኤ ቤት ይሆናል።

ይህም ጉባኤ ቤት ለመጽሐፍ እውቀት ወደ ጎንደር ጎጃም የሚጓዙ የአከባቢ አገልጋይን ድካም ሙሉ በሙሉ ያስቀራል ተብሎ ይጠበቃል።

የጉባኤ ቤቱ የመምህራን እና ደቀመዛሙርታት መኖርያ ቤት፣ ምግብ ቤት፣ መማርያ ክፍል እና ሌሎች ተጨማሪ ክፍላትን ያካተተ ነው ።