Get Mystery Box with random crypto!

‏ጎንደር ታላቅ አሊም አጣች። ‏ ሸህ ጀማል አደም ሀገር ውስጥም በሰፈር ቂራዓት በውጭም በሱዳን አ | NidaTube -ኒዳ ቲዩብ

‏ጎንደር ታላቅ አሊም አጣች።
‏ ሸህ ጀማል አደም ሀገር ውስጥም በሰፈር ቂራዓት በውጭም በሱዳን አፍሪካ ዩንቨርስቲ በቂርዓት አቀባበላቸው ፈጣንና ሀፊዝ ነበሩ። የጎንደር ከተማ ዑለማ ም/ቤትን በዘመናዊ አሰራር የተሻለ ሀሳብ በማምጣት ጥሩ እቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩና የጎንደር ሙስሊሞችን ግፍ በአደባባይ የተጋፈጡ ታላቅ አሊም ነበሩ። አባ-ሼህ ጀማል አደም - ከላቁ የእኛ-ዘመን ዑለሞች መካከል ተጠቃሽ ነበሩ።
‏በጎንደር-ከተማ ሚና መስጂድ፣ ኢማም፣ ኸጢብና ዋዒዝ ነበሩ።

‏የጎ/ከ/ዑለ/ም/ቤትን በነጻ፣ ለሁለት ዓመታት በፀሀፊነት አገልግለዋል። ለአምስት ዓመታት የስራ አስፈጻሚ አባል ኾነው ቆይተዋል። ለውጥ ፈጥረዋል። ‹ሼህ ጀማል አደም› ቢኾንም ስማቸው፣ በ“ሼህ ጀማል ገበሬው” ነው የሚታወቁ። በእርግጥም! የነህው፣ የሶርፍ፣ የመንጢቅ፣ የሉጛ ገበሬ ነበሩ። የዲን ገበሬ ነበሩ። በወሎና በጎንደር፣ እንዲሁም በሱዳን ሀገር ተዟዙረው ሰፊ ዒልም ያካበቱ ታላቅ ዓሊም ነበሩ።

‏ሼህ ጀማል ከወራት በፊት ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው በትናንትናው ዕለት ለህልፈት በቅተዋል። መልካም ስራቸውን አላህ ይቀበላቸው። ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእኛም መፅናናት ይኹን። አላህ መልካሙን ተተኪ ይስጠን!!!
اللَّهُمَّ اغْفِرْ لَهُ وَارْحَمْهُ، وَعَافِهِ، وَاعْفُ عَنْهُ، وَأَكْرِمْ نُزُلَهُ، وَوَسِّعْ مُدْخَلَهُ، وَاغْسِلْهُ بِالْمَاءِ وَالثَّلْجِ وَالْبَرَدْ، وَنَقِّهِ مِنَ الْخَطَايَا كَما نَقَّيْتَ الثَّوْب الأَبْيَضَ مِنَ الدَّنَسِ، وَأَدْخِلْهُ الْجَنَّةَ، وَأَعِذْهُ مِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ وَعَذَابِ النَّارِ