Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል? ፈተናው በመጪው ሐምሌ ይሰጣል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ | ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ፈተናው በመጪው ሐምሌ ይሰጣል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ እስከአሁን የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ትክክለኛና ቁርጥ ያለ ቀን ይፋ አልተደረገም።

የፈተናው ቀን ይፋ የሚደረገው በማዕከል በኩል ከትምህርት ሚኒስቴር / ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሲሆን ይህም ለህዝብ በይፋ በመገናኛ ብዙኃን ይነገራል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የተፈታኞች የበይነ መረብ ምዝገባ /online Registration/ አፈጻጸም ግምግማ ባለፈው ሳምንት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከውይይቱ የተገኙ ሀሳቦችም በሰነዱ ተካተው በድጋሚ ለውይይት እንደሚቀርብና ሲጸድቅ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነግሯል።

@News_for_student
@News_for_student