የቀድሞው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጫላ ዋታ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል፡፡ የፍትሕ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ምክር ቤቱ የብልፅግና ፓርቲን በመወከል የምክር ቤቱ አባል የሆኑትን ጫላ ዋታ (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብት አንስቷል። ጫላ ዋታ (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የመንግስት ግዢ ስርዓትን ሳይከተሉ የተለያዩ ግዢዎችን ፈጽመዋል በሚል በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው ነው፡፡ @News_for_student @News_for_student 2.2K views16:29