Get Mystery Box with random crypto!

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚያ | ትምህርት ሚኒስቴር

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚያ 15 ይከናወናል።

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ለዚህ ዓመት ፈተና ምዝገባ የሚካሄደው፤ ከመጪው ረቡዕ መጋቢት 20 ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 15፤ 2015 ድረስ እንደሆነም አገልግሎቱ አሳውቋል።  የዘንድሮው ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ የሚወሰነው፤ ለአንድ ወር ገደማ ከሚቆየው የተማሪዎች ምዝገባ መጠናቀቅ በኋላ መሆኑን

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን አንድ ሚሊዮን ገደማ ተማሪዎች በመደበኛ እና በግል ለፈተናው ሊቀርቡ ይችላሉ ተብሎ እንደሚገመት በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተማሪዎች ውስጥ 850 ሺህ የሚሆኑት መደበኛ እንደሚሆኑም ተገምቷል።

ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡም ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

ያልተመዘገበ ተማሪ የ 2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እንደማይፈተንም ዶ/ር እሸቱ ገልፀዋል።

@News_for_student
@News_for_student