Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ መክፈል ሊጀምሩ ነው። የገንዘብ ሚኒ | ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ መክፈል ሊጀምሩ ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሰራተኞች ውዝፍ ደመወዝ መክፈያ እና የአንድ ወር የሥራ ማስኬጃ በጀት ባለፈው አርብ መጋቢት 01/2015 ዓ.ም እንደፈቀደላቸው ዩኒቨርሲቲዎቹ ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ላላፉት 20 ወራት በዩኒቨርሲቲዎቹ ለሚሰሩ ሰራተኞች ደመወዝ አለመከፈሉን የመቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የፌደራል ተቋማት ለሆኑት አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ሰራተኞች የደመወዝ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ መተላለፉን የገንዘብ ሚኒስቴር ምንጮች አረጋግጠዋል።

“የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስላልተመሰረተ ለክልሉ የተላከ ገንዘብ የለም” ሲሉም የሚኒስቴሩ ምንጮች አክለዋል።  

የደመወዝ ክፍያው በ2015 በጀት ዓመት ከታህሳስ እስከ የካቲት ያሉትን ሦሥት ወራት የሚሸፍን ነው።

ውዝፍ ክፍያው የዩኒቨርሲቲዎቹ ሰራተኞች የነበሩ እና በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ሰራተኞችን አይጨምርም ተብሏል።

@News_for_student
@News_for_student