Get Mystery Box with random crypto!

@Newayekidisat @Newayekidisat 13ቱ ሕማማተ መስቀል 7ቱ የመስቀሉ ቃላት 7ቱ ተዐ | ንዋየ ቅድሳት

@Newayekidisat
@Newayekidisat
13ቱ ሕማማተ መስቀል
7ቱ የመስቀሉ ቃላት
7ቱ ተዐምራት
5ቱ ችንካሮች


#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል

1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ
መውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ
መረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር
መላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)

#ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡
46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር
በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት
እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ
(ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡
30)

#ሰባቱ_ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ
የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
+ + + + +
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ
ችንካሮች
1. #ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. #አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን
ቸነከሩት
3. #ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን
ቸነከሩት
4. #አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን
ቸነከሩት
5. #ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

@newayekidisat
@newayekidisat