Get Mystery Box with random crypto!

ለውድ ወላጆች እና ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት በኢትዮጵያ በዓይነቱ የተለየ ነው የተባለው | Neway Challenge Academy-Official Account

ለውድ ወላጆች እና ተማሪዎች
በተያዘው ፕሮግራም መሰረት በኢትዮጵያ በዓይነቱ የተለየ ነው የተባለውን የሳይንስ ሙዚየም የነዋይ ቻሌንጅ ተማሪዎች ዛሬ ጉብኝት አድርገዋል። ይህንን ጉብኝት ያደረጉት ተማሪዎች ከ1-8 ክፍል ደረጃ ያሉ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ክለብ አባላት ሲሆኑ በጉብኝቱ ወቅት አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የፈተሹበት፣ ለተለያዩ ፈጠራዎች መፍለቂያ እና መንደርደሪያ የሚሆኑ ሀሳቦችን ያገኙበት እንደሆነ ተማሪዎቹ ገልጸዋል። ትምህርት ቤቱ ባስቀመጠው ፕሮግራም መሰረት በቀጣይም ሌሎች ተማሪዎች ይህንን አስደናቂ እና ተማሪዎችን ለተግባር የሚያነሳሳ ሙዚየም እንዲጎበኙ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ለማሳወቅ እንወዳለን።
ትምህርት ቤቱ!