Get Mystery Box with random crypto!

የተከበራችሁ ወላጆች እና ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ካሪኩለም በ2015 ዓ.ም. በትግበራ ላይ | Neway Challenge Academy-Official Account

የተከበራችሁ ወላጆች እና ተማሪዎቻችን
አዲሱ የትምህርት ካሪኩለም በ2015 ዓ.ም. በትግበራ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ሲባል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ቀደም ብሎ ለመማር ማስተማር ሂደቱ ሲጠቀምባቸው የነበሩትን መጽሀፍቶች ከ1ኛ ክፍል አስከ 8ኛ ክፍል የቀየሩት መሆኑን አስታውቀዋል። መጽሀፍቶቹ በአሁኑ ወቅት በህትመት ሂደት ላይ ስለሆኑ ለተማሪዎች ሊሰራጩ አልቻሉም። መጽሀፍቶቹ ታትመው እስኪሰራጩ ድረስ ወላጆች ከዚህ በታች በየክፍል ደረጃ በከፊል የላክነውን ኤሌክትሮኒክስ ቅጂ እንድትጠቀሙ እናሳውቃለን።
ከሰላምታ ጋር
ት/ቤቱ