Get Mystery Box with random crypto!

NESUHA calligraphy and poems

የቴሌግራም ቻናል አርማ nesuhaawel_poem — NESUHA calligraphy and poems N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nesuhaawel_poem — NESUHA calligraphy and poems
የሰርጥ አድራሻ: @nesuhaawel_poem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 581
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የተከፈተው ለ ካሊግራፊ እና የግጥም ወዳጆች ነው
በቻናላችን ➊ ግጥም
➋ ካሊግራፊ
አላህ በሰጠን ችሎታ የምናቀርብ ይሆናል
የፍሬም ስራዎቼን መግዛት ለምትፈልጉ

@Nesuhapoem_bot
እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት @Nesuhapoem_bot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-28 07:12:01 ሰወችየ አስተያየታችሁን እየሰጣችሁ

@Nesuhapoem_bot

ወይንም leave a comment ሚለው ላይ ፃፍ ፃፍ አድርጉልን

እናመሰግናለን


http://t.me/Nesuhaawel_poem
104 viewsNesuha, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 06:44:14 #ምንሽን

(ነሱሀ አወል)

እንደ አሳማሚሽ ዝም ብየ በማየት ውስጥ
........

ምን አይቶብኝ ይሆን? ከውብ ፈገግታሽ ላይ መአት እንባ የተመዘዘው?...ከደስታሽ ክምር ውስጥ ሀዘን የተቀላቀለው?..ለራስሽ ተርፎ ለሰው ያጋራሽው ደስታ ፍቅፋፊ እንኳ ላይቀረው የተሰናበተሽ...ምኑን አሳየብኝ?ምንሽን ልደግፍሽ?...የቱ ጋር ነው ያሳመሙብኝ?...የቱ ጋሽንስ እፍፍፍ እያልኩ ከግለቱ ለጥቂት ላሳርፍሽ?...የቱጋ ልከክልሽ በክራንች ጥርስ የሚቧጥጥሽ የቱ ጋር ነው?...እዚህ ብለሽ ላትጠቁሚም ዳግም አስረውሻል? ታዲያ መክሰሬን ምን ልበል?

........

⎡ በወዳጅ ስቃይ ውስጥ የምንታመመው ህመም ቀላል አይደለም...ያሽሸው እንጂ ሳይመጣ⎤


http://t.me/Nesuhaawel_poem
99 viewsNesuha, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 16:32:15
http://t.me/Nesuhaawel_poem
120 viewsNesuha, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 15:12:16
ቅርባችን መሰሎን ልንዳስሰው ስንዳዳ ስንቱ ደብዛው ጠፍቶ አስደነበረን .......!? ስንቱ ተጣግቶን እንዳልነበር ልንጨብጠው ስንሽት እንደጉም ብንንንን...... አለ ፤ ሰንቱ.....!?ለምልከታ ቅርብ የመሰለ ለመዳሰስ ሲሹ ግና ዉሉ ማይጨበጥ ስንት አስማተኛ ህልም አለ ?
ስንቴ አምነኸህ ስትጠጋው፡ ስንቴ ነው የከዳህ ግን?

samiya T



14/02/14

@samyalink
@samyalink
@samyalink
92 viewsNesuha, 12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 15:08:28
#ደህና_ሁን_ደህና_ሁኚ


(ነሱሀ አወል)

ስትፈልጊ ብቻ ከጎንሽ ልነኝ ሻትሽ...በፈለግከው መንገድ ብቻ ላወራህ ተመኘህ...የአልባሶችሽ አድናቂ ሆኜ መራቆቴን ወደድሽ...የልብህን መሻት እንድሞላ መሻቴን ገፈተርህ...አማረብሽ ልልሽ ብቻ ከጅለሽ ማማሬን አቆሸሽ...ላይህን ሸፍነተህ ታማኝ ልቤን ቧጠጥከው...ሌላም...ሌላም....ሌላም..እናም '' ደህና ሁኚ / ደህና ሁን''


http://t.me/Nesuhaawel_poem
102 viewsNesuha, edited  12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 14:57:36 #poem_324

(ነሱሀ አወል)

መስሎሻል ...!

ያወቅሽኝ
ከጥግ እስከ ጥጌ፣
ከስሜ በስተቀር
አታውቂም እላለሁ
በፊዘት ፈግጌ።

እንዴት ስትይ እቱ...!

ባልተገለጥሁበት
አንብበሽ ጨረሽኝ
ገፆቼን በንጥል፣
አታውቂውም መሰል
አንድ እያሳየሁሽ
መቶ ስገነጥል።

አወይ ሞኝነትሽ
የተበላ ጊዜ
የፈጀሽው በኔ፣
እንኳን ላንቺ ቀርቶ
ሙሉ አልተገለጥሁም
እኔው ራሴ ለኔ።



http://t.me/Nesuhaawel_poem
100 viewsNesuha, edited  11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 19:36:20 #poem_323

(ነሱሀ አወል)
......

''አንድ ልጅ ነበረች
እንትና ሚሏት፣
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብላ
ንፋስ ወሰዳት።''

ብለን ያዜምንላት
ያቺ ልጅ ምን ዋጣት?፣
ንፋሱስ ወስዶ
ወዴት አስቀመጣት?።

ስለሷ ልጅ ሳስብ..!

ተወሰደች ብቻ
ተገጥሞላት ግጥም
ተዚሞላት መዝሙር፣
ፈላጊዋ ጠፋ
የቀበና ውሀን
ምንጭ ለመዘከር።

የት ነሽ የሚል ጠፋ...!

ንፋሱን የሚከስ
ወየት ወሰድካት ሚል፣
ነገሩ በሀገሬ
የሚያነሳ የለም
ከስክሶ እንደሚጥል።

''የቀበና ውሀ
ምንጩ ደፈረሰ፣
ምንም ሳላጠና
ፈተና ደረሰ።''

ይላል ለመጥፊቷ
የት ነች እንዳትባል፣
ልቤ የት ሄዳ ነው?
ብሎ እያሰበ
እንደምን ያነባል?።

ልውደቅ ከትምርቱ
ምን ገዶኝ ለጥናት
ይለፈኝ ፈተና፣
ንፍስ የወሰዳት
የት አለች እንትና?።


http://t.me/Nesuhaawel_poem
108 viewsNesuha, edited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 16:37:41
nesuha awel

price - 600ETB

በትእዛዝ ማሰራት ለምትፈልጉ
@Nesuhapoem_bot ላይ አናግሩኝ


http://t.me/Nesuhaawel_poem
106 viewsNesuha, 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ