Get Mystery Box with random crypto!

አንች ናፋቂ አንቺ ስደተኛ አንች ባህታዊ አይዞሽ السلام عليكم ورحمة الله وبركا | ነሲሐ ለሱኒዋ እህቴ!!

አንች ናፋቂ አንቺ ስደተኛ አንች ባህታዊ
<><><><><>አይዞሽ<><><><><>

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

አንች በሰው አገር ያለሽ እህት ሆይ!! አይዞሽ ያልፋል በጣም አታስቢ አትጨናነቂ


ይገባኛል ወንዝሽ እንደሚናፍቅሽ ጓደኞችሽ እንደሚናፍቁሽ ቤትሰቦችሽ እንደሚናፍቁሽ ሌላው ቀርቶ ላሞቹ በሬወቹ እንደሚናፍቁሽ ይገባኛል ግን ያልፋል።

በተለይ ወደ ሰው አገር ከሄድሽ ቡሃላ የእናት የአባት የወንድም የእህት ሞት ከሰማሽ ሀዘኑ ከባድ ነው።

ቢሆንም ግን ስለሚያልፍ ዋጥ አርገሽ አሳልፊው በእርግጥ የቤትሰብ ሞት ስሜቱ ከባድ ነው

ይሁን እንጂ የመከራ ማሲንቆ እያንጎራጎርሽ ራስሺን ከመጉዳት የኢማን መቀነት ታጠቅ ብለሽ አሏህ እንድምራቸው ዱአ እያደረግሽ በትዕግስት ስራሽን ብትሰሪ ይሻላል።

አንዳንዴ ሳታስቢው በናፍቆት ሰመመን ገብተሽ እንባሽ በጉንጮችሽ ላይ ሲወርዱ ልታይ ትችያለሽ

ግን አታብሰልስይው ቶሎ ብለሽ ቁርኣን ወይም ሐድስ ወይም ሙሓደራ ከፍተሽ አዳምጭበት ወይም ቁርኣን ቅሪበት

ይህ ካልሆነ ግን ተጎጂይቱ አንችው ነሽ ቆንጆ ማለት ትዝታና መከራ በሚመጣበት ጊዜ ታጠቅ ብሎ በትግስት የሚያሳልፍ ነው

አሏህ ይርዳሽ አሏህ ከመከራ ዜና ይጠብቅሽ

t.me/abumuazhusenedris
t.me/abumuazhusenedris