Get Mystery Box with random crypto!

#እስር_ቤት_ሆስፒታል_እና_መቃብር ቦታ ሄዳችሁ ታውቃላችሁ አንድ ሀብታም ሰው መስኮቱን ተመለከተ | NINA PICTURES

#እስር_ቤት_ሆስፒታል_እና_መቃብር
ቦታ ሄዳችሁ ታውቃላችሁ

አንድ ሀብታም ሰው መስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ፤ እንዲህ አለ፦

"ተመስገን አምላኬ ድሃ እንኳ አልሆንኩ!"

ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳናው ላይ የሚራመድ ሰው አየ፤ እርሱም እንዲህ አለ፦

"ተመስገን አምላኬ እብድ እንኳ አልሆንኩ!"

እብዱ ሰውዬ ወደ ፊት ተመለከተና አንድ አምቡላንስ አየ። አምቡላሱ ውስጥም በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ፤ እንዲህም አለ፦

"ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ!"

ከዚያም የታመመው ሰውዬም በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው ሬሳ ተመለከተ። በማስከተልም እንዲህ አለ፦

"ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ! ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና!"

ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም?!

ሕይወትን በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ!

1. እስር ቤት
2. ሆስፒታል
3. መቃበር

ምክንያቱም፦

~ በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ!

~ በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ!

~ በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ!

ዛሬ የምንሄደው መንገድ፤ የነገ ሕይወታችን መሰረት ነው። ስለዚህ ትሁትና አመስጋኝ እንሁን!

ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን ይመስገን

NESHO PICTURES
@mirazh_94