Get Mystery Box with random crypto!

ምዑዝ miuz

የቴሌግራም ቻናል አርማ negeremiuz — ምዑዝ miuz
የቴሌግራም ቻናል አርማ negeremiuz — ምዑዝ miuz
የሰርጥ አድራሻ: @negeremiuz
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 182
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ ትምህርቶችን ጠቃሚ ምክረ አበውን እኔዲሁም ለጥያቄዎት መልስ ያገኙበታል 0923642766 ላይ ይጻፉልን።

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-02 10:36:48 ለ2 ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው የምክክር ጉባኤ ባለ7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ!!
***

               (ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም
                 አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከ
ት አዘጋጅነት ከሰኔ 23-24 ቀን 2014 ዓ.ም ለ2 ቀናት በአብነት ት/ቤት መዳከም እና ፍልሰት እንዲሁም በመምህራኑ ትኩረት መነፈግ ዙሪያ ሲካሄድ የሰነበተው የአብነት ት/ቤት መምህራን የምክክር ጉባኤ ባለ7(ሰባት)
ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል።

በምክክር ጉባኤው የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በብዙ ችግሮችና ተግዳሮቶች የተተበተበ ሰለሆነ በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ተጠምደን ስለነበር ሁኔታዎች ተመቻችተው እስካሁን ድረስ ሊቃውንቱን አላወያየናችሁም ነበር ብለዋል።

አክለውም የቤተክርስቲያንን ችግር ለመፍታት ከእናንተ በላይ ባለድርሻ አካል የለምና ወደፊት ችግሮችን  በጥልቀት እና በተከታታይነት የምንፈትሽበት ሰፊ የምምክርና የውይይት መርሐ ግብር እናሰዘጋጃለን ሲሉ ብፁዕነታቸው ተደምጠዋል።

አሁን ሀገረ ስብከታችን እየተከተለ ባለው የውስጥ አሠራር የቤተክርስቲያንን ሊቃውንት ይቅርና የትኛውም ቤተክርስቲያንን ተጠግቶ የሚሠራ ሰው ባለበት ሥፍራ ተከብሮና ተረጋግቶ እንዲሠራ ማድረግ ነው ያሉት ደግሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ ቆሞስ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ ናቸው።

ለሁለት ቀናት በቆየው ጉባኤ አገልግሎት ተኮር የሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በጉባኤው ተሳታፊ መምህራን በኩል የቤተክርስቲያንን አስተምህሮና ዕውቀት ከማስቀጠል አንጻርና ተገቢውን ትኩረት ከአለማግኘት አንጻር በርካታ ጥያቄዎች ተነሥተው፣ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም አጠቃላይ የጉባኤው ኩነቶች የተዳሰሱበት ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በመ/ብ ሳሙኤል ደምሴ የሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ዋና ክፍል ኃላፊ ተነቦ በብፁዕነታቸው ጸሎት ጉባኤው
ተፈጽሟል።



ሙሉ የአቋም መግለጫው ከዚህበታች እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የአቋም መግለጫ

1.  ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቆማና ጸንታ የቆየችው በሊቃውንት የእምነት ጽናት፣መንፈሳዊ ሕይወት መሆኑ ይታመናል፡፡ በመሆኑም ለወደፊት የጉባኤ መምሕራንን ያሳተፈና ያካተተ አሠራር በሀገረ ስብከቱ በኩል እንዲሰፍን እየጠየቅን፣ አሁን በትምሕርትህ ማሰልጠኛ ዋና ክፍል ለተደረገው ሊቃውንቱን የማወያየት ተግባር ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

2.ሌሊት በማሕሌት፣ ቀን በፍትሐት በትርፍ ሰዓታችን ደግሞ ደቀ መዛሙርቱን በማፍራት እየደከምን የመምሕራኑ ደመወዝ ካስተማርናቸው ዲያቆናት ከድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ማነሱ የሊቃውንቱን ሞራል የሚነካ አገልግሎቱን የሚያዳክም ስለሆነ የደመወዝ እስኬል እንዲሰራልን እንጠይቃለን፡፡

3. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እስካሁን የቆየችው ያለደመወዝ ወንበር ዘርግተው ጉባኤ አስፍተው ባሉ መምሕራን መሆኑ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም እኛ በአዲስ አበባ የምንገኝ የጉባኤ መምሕራን በተመደብንበትና በተማርነው ሙያ  ጉባኤ ዘርግተን ለማስተማር ቃል እንገባለን፡፡

4. ሳይማሩ የሊቃውንቱን ስም የሚወስዱ በዕውቀት በተራቀቁ ሊቃውንት ስም የሚጠሩ ለሙያው ያለውን ክብር የሚያሳጣ ሊቃውንትም ክብራቸውን የሚያሳንስ ስለሆነ ለወደፊቱ እንዲህዓይነቱ ስም ባልተሰጣቸው ሥልጣን የሚሰጡ አገልጋዮች እርምት እንዲሰጣቸው እየጠየቅን ብፁዕ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ ለገዳማትና ለአድባራት አባታዊ መመሪያ በጽሑፍ እንዲያስተላልፉልን በታላቅ አክብሮት በልጅነት መንፈስ እንጠይቃለን፡፡

5.ድጓውን፣ ቅኔውን አቋቋሙን ዝማሬ መዋስዕቱን እንደባጣ ቆይኝ የሚቆጥሩትን፣ ሳይማሩ ተምረናል የሚሉትን በስማችን የሚነግዱትን፣ ድምጽ ማጉያ የሚዘጉትን  በማስተማር፣ በመምከር የበኩላችንን ጥረት በማድረግ ማሕሌቱ እንደጥንቱ ለካህናትና ለምዕመናን ተደማጭ ለማድረግ በጋራ እንሰራለን፡፡

6. በቤተ ክርስቲያናችን የማስመስከሪያ ጉባኤ ቤቶች በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ የታወቁና ጥንትም የነበሩ ናቸው፡፡ አሁን ግን በየደብሩ የሚሰጡ የአብነት መምሕራን ምስክሮች አግባብ ካለመሆኑም ሌላ የሊቃውንትን እውቀት የሚያሳንስ ስለሆነ ይሕ እንዲታረም እየጠየቅን፣ በማሕሌት ወቅት የማሕሌቱን ክብር የሚያሳንስ የከበሮ አመታት ዘይቤ እንዲስተካከል በጋራ ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡

7. ሊቃውንት በዶግማ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በአጠቃላይ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በመሳተፍ የመወሰን ድርሻ ስላላቸው አስፈለጊ መሆኑ ታምኖበት አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በማዕከል ያለ የሊቃውንት መገኛ በመሆኑ ለወደፊት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ ጉባኤ ተዘጋጅቶ በገጠር ላሉ መምሕራን ጭምር የመፍትሔ ሀሣብ ለማቅረብ እንድንችል መርሐ ግብር እንዲመቻችልን እየጠየቅን ይህንን ባለ 7 የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

             ሰኔ 24 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም.

                
40 viewsKalkidan cherent, edited  07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:19:29 አገልግሎት ያለ ፍቅር የሚከናወን ከሆነ ደረቅና ድግግሞሽ ከመሆኑም በላይ ያለ መንፈስ ወይም ያለ ፍሬ ይቀራል ፡፡ ይህም ማለት እንዲሁ እውቀት ማስተላለፍ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው፡፡
ብጹዕ አብነ ሽኖዳ
55 viewsKalkidan cherent, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:19:29


አንተ ሰው !

ቃለ እግዚአብሔርን ተማር !
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር !
ኹልጊዜ ተማር !
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ።
ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፡፡
ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን
እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡
ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች !!!

"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"
55 viewsKalkidan cherent, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 05:53:16
44 viewsKalkidan cherent, 02:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 11:45:48 "የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ   ይሰፍራል÷ ያድናቸውማል።"
                                (መዝ.33÷7)


የዛሬው የሰኔ 12 የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል፣የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ሰዎች ማዳኑን የገለጠበት ዕለት ነው።

አፎሚያና ባሕራን ከእነቤተሰባቸው እግዚአብሔርን በመፍራት የሚታወቁ ሰዎች ሲሆኑ ከደረሰባቸው ፈተና ሁሉ በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት የዳኑበትና የእግዚአብሔር ትድግና በመልአኩ በኩል የታየበት ነው።

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል÷ ያድናቸውማል።" ማለቱ  ለዚህ ነው (መዝ.34÷7)። እግዚአብሔርን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ የእግዚአብሔር መላእክት ጥበቃ አይለይም።

ልጆቼ ኑ÷ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።"የተባለው ለዚህ ነው(ቁ.11)። የመላእክት ጥበቃና አዳኝነት፣ ከሰው ልጆች እግዚአብሔርን መፍራት ጋር የተሳሰረ መሆኑን የዳዊት መዝሙር ያስረዳል።

እግዚአብሔርን መፍራት የሰው ልጆች ድርሻ ሲሆን፣ መጠበቅና ማዳን ደግሞ የመላእክት ድርሻ ነው (መዝ. 91÷ 11-12)።

የተሣንበት ርእሰ ጉዳይ እግዚአብሔርን የምንፈራው ስንቶቻችን ነን? የሚለውንም እንድናስብ ያደርጋል። ምክንያቱም የመላእክቱ ጥበቃና ማዳን እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር የአንደ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ስለሆነ ነው።

ሐዋርያው ቅዱስጳውሎስም ስለ መላእክት አገልግሎት በገለጸበት መልእክቱ፦ "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገልሉም መናፍስት አይደሉምን?" ብሏል (ዕብ.1÷14)።

ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ሰዎች ደግሞ እግዚአብሔርን ማመንና መፍራት አለባቸው።

በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፣ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ÷ አልቻላቸውምም።" (ራእ.12÷7)።

አጠር ባለ መልኩ በደግነትና በመልካምነት የምትታወቀው አፎሚያና በባሕር  ውስጥ ተጥሎ የተገኘውን ባሕራንን አምላካችን እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን ልኮ ከጠላት እጅ ታድጓቸዋል።

እኛም በሕይወታችን እግዚአብሔርን ካከበርነው በክፉዎች የምንወድቅና የምንሞት ብንመስልም የማይጥለን አምላክ የሞታችንን ደብደቤ ወደ ሕይወት እንደሚቀይርልን አምነን እንኑር። የባሕራንንና አፎሚያ ወዳጅ ቅዱስ ሚካኤል በጥበቃና ረድኤቱ ዘወትር ከኛ ጋር ይሁን አሜን።

የእግዚአብሔር ቸርነት የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን!

      
     እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!
96 viewsKalkidan cherent, edited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 05:52:20 Live stream finished (15 hours)
02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 14:05:02 Live stream started
11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:14:45
83 viewsKalkidan cherent, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:14:45
74 viewsKalkidan cherent, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:14:44 ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በመገኘት አዲሱን ቢሮ ጎብኝተው የሥራ መመሪያ ሰጡ!!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++

                 (ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም
              (አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ)

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በመገኘት አዲሱን ቢሮ ጎብኝተው የሥራ መመሪያ ሰጡ።

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የቢሮ አድራሻ ቅያሬ አድርጓል።

ከዚህ በፊት አራት ኪሎ በሚገኘው በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ሕንጻ ሲገለገል መቆየቱ ይታወቃል።

ክፍለ ከተማው የተከራየው አዲሱ ቢሮ  አድራሻው ስድስት ኪሎ ሲሆን ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ሕንጻ ላይ ነው።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቦታው በመገኘት ቢሮውን ጎብኝተዋል፤በጸሎትም ባርከዋል።

መ/ሰ የቻለው ለማ የአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለአዲስ አበባና ለጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በመርሐ ግብሩ ላይ ለተገኙት በሙሉ "የእንኳን ደህና መጣችሁ" መልእክት አስተላልፈዋል።

የቢሮ አድራሻ መቀየር ያስፈለገበት ምክንያት የበፊቱ ቢሮ በቤተ መንግሥት አጠገብ በመገኘቱ ባለጉዳዮችን በሚፈለገው መጠን ለማስተናገድ አለመቻሉን ጠቅሰዋል።  

በመሆኑም ጉዳዩን ለብፁዕነታቸው በማስረዳት ፈቃድ ካገኙ በኋላ በክፍለ ከተማው ሥር ከሚገኙ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ከመከሩ በኋላ ኮሚቴ ተዋቅሮ  ለክፍለ ከተማው አማካይ ቦታ ተፈልጎ እንደተከራዩ ክቡር ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

አያይዘው ቢሮ የቀየርንበት ዋናው ዓላማችን ለራሳችን ምቾት ሳይሆን የቤተክርስቲያንን አገልግሎት በተገቢው መልኩ ለማከናወን፣ የተሰጠንን  ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣትና ባለጉዳዮችን በተቀላጠፈ መልኩ ለማስተናገድ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።

ሊ/ኅ ዳዊት ታደሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጆችን ወክለው ባስተላለፉት መልእክት መ/ሠ የቻለው ለማ መምራት የሚችሉ፣ የተሰጣቸውን  ኃላፊነት በአግባቡ የሚወጡ፣ ታታሪና ብርቱ አገልጋይ ናቸው በማለት ገልጸዋል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን "ይህ ቀን የምስጋና ቀን ነው" ብለዋል፤ ለሥራ አስቸጋሪ ከሆነበት ቢሮ ወደ ዚህ አመቺ ወደሆነበት ቢሮ መምጣት ለሥራ መነሣሣትን የሚጠቁም መሆኑን አውስተዋል።

የሥራ ፍላጎት ያለው ኃላፊ በአስቸጋሪ ቦታና ወቅት እንኳ የሚሠራ ቢሆንም ምቹ ሁኔታን ካገኘ ደግሞ የበለጠ ይሠራል ብለዋል።

ዋናውና ትልቁ ነገር የተሰጣችሁን ኃላፊነት በአግባቡና በታታሪነት በመወጣት ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ ልትሠሩና ፍሬ ልታፈሩ ይገባል ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውንና መመሪያ አስተላልፈዋል።

ሁሉም ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ወደፊት ከኪራይ ቢሮ ተላቀው የራሳቸው ቢሮ እንዲኖራቸው ተባብረን በዕቅድ እንሠራለን ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነመልከጼዴቅ፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊ/ጉ ቆሞስ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍል ኃላፊዎች፣ የአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ሠ የቻለው ለማ፣ የክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የክፍለ ከተማው ቤተክህነት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት ተገኝተዋል።

     
57 viewsKalkidan cherent, edited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ