መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፀም ትኩረት መደረግ ያለባችሁ ጉዳዮች ==================== ማንኛውም መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፅሙ ትኩረት ማድረግ ያለባችሁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ o በመጀመሪያ ይዞታው ህጋዊ ካርታ (የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት)ና ህጋዊ ፕላን ያለው መሆን አለበት፡፡ o በሻጭ እጅ ያሉ ሰነዶችና በክ/ከተማው በመዝገብ ቤት በሻጭ ስም ያለ የይዞታ ማህደር ጋር ሰነዶች በትዩዩ አንድ አይነት መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡ በተለይም በካርታው ላይ ያለው የካርታ ቁጥርና በክ/ከተማ መዝገብ ቤት ያለው ቀሪ ካርታ ቁጥር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ o የይዞታ ማህደሩ ከእዳ፣እገዳና ሌሎች ክልከላዎች ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የሊዝ እዳ ገዥው እስከ እዳው መግዛት የሚፈልግ ከሆነ እዳውን ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ o ትዳር ያለው ከሆነ ከወሳኝ ኩነት የትዳር ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፡፡ ትዳር የሌለው ከሆነ ይህንን የሚያረጋግጥ መረጃ ያስፈልጋል፡፡ o ህጋዊ የሽያጭ ውል ከፍትህ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ o በውክልና የሚሻሻጡ ከሆነ ውክልናው ህጋዊ መሆኑን ውክልና ከሰጠው የፍትህ ተቋም ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ o በተጨማሪም በአካል ወደ ሚሸጠው ቤት ሂዶ ቤቱን በአካል ማየትና ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ o ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ማለትም ይዞታው ወደ ፊት ለመኖሪያ ወይስ ወደ ንግድ መቀየር ይቻላል የሚለውን ሀሳብና ከግንባታ ከፍታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን ማማከርና ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ via ቢቡኝ 782 views14:40