Get Mystery Box with random crypto!

አንድ 'ነብይ'ላቡን የጠረገበትን ሶፍት ፔፐር 'ከፈለክ በውሃ ከፈለክ በምግብ ሶፍቱን ብላው' ብሎ | ነገረ ወንጌላውያን

አንድ "ነብይ"ላቡን የጠረገበትን ሶፍት ፔፐር "ከፈለክ በውሃ ከፈለክ በምግብ ሶፍቱን ብላው" ብሎ ለአንድ ምዕመን ሲሰጥና ምዕመኑ "ላብህን የጠረክበትን ሶፍት በልቸ ከኩላሊት ህመም ተፈወስኩ" ሲል የመሰከረበትን ቪዲዮ ተመለከትኩ! አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ልክ አይደሉም ሲባሉ በቤታቸው ከሚፈፀመው ክብረ ነክ ወንጀል ይልቅ ገና ለገና እምነታችን ተነካ በሚል ስሌት "እግዚአብሔር አሰራሩ ልዩ ልዩ ነው" "በመንፈስ ካልሆኑ አሰራሩን መረዳት አይቻልም" ምናምን ይላሉ! ጥቅስ ያጠጋጋሉ! የማንንም የግል አረዳድ እምነት አከብራለሁ ... ግን እነዚህ "ነብያት" ዛሬ የፊታቸው ቆሻሻ በተጠረገበት ሶፍት በኩል እግዚአብሔር ተዓምር ሰራ ካሉ ፣ ነገ ሌላ ነገራቸውን የጠረጉበትን ሶፍት ለዚህ ምዕመን ቢያቀርቡለት እልል ብሎ እየከፈለ ይወስዳል ፣ለምስክርነትም ይቆማል!

ብቻ ይደክማል! ከማንም በፊት የቤቱ ሰዎች ይሄን ነገር አንድ በሉት! "እኔን ማን ፈራጅ አረገኝ" በሚል አጉል መንፈሳዊነት ስትሸበቡ ነገ በሌላው ዓለም ስንሰማው የኖርነው በእምነት ስም የሚፈፀም ዘግናኝ ግፍና ሰቆቃ በቤታችሁ እንዳይሆን ከእምነት ቤቱ አልፎ እንደአገር የሞራል ጥያቄ እንዳያስነሳ ሳይቃጠል በቅጠል

አሌክስ አብርሃም