Get Mystery Box with random crypto!

10 ለማስረጃነት የበቁ የትንሣኤው ተጨባጭ መረጃዎች! ከ2 ሚሊንየም በፊት ኢየሱስ በአይሁድ ባሕ | ናዝራዊ Tube

10 ለማስረጃነት የበቁ የትንሣኤው ተጨባጭ መረጃዎች!

ከ2 ሚሊንየም በፊት ኢየሱስ በአይሁድ ባሕል በታወቀ ሥፍራ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ እያየ በአደባባ ራቁቱን ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ከተቀበረም በኋላ፣ "ይነሣል" የሚል ወሬ ቤተመንግሥትን ስላሰጋ ትልቅ ድንጋይ በመቃብሩ ላይ ተደረገ፤ በማህተም ታትሞ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ ይደረግ ዘንድ በመንግሥት መታዘዙን በወንጌላት ተጽፎአል፡፡ በቃሉ " እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሳው፤ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም"ና (ሐዋ. 2፡ 24) እንደተባለው የትንሣኤ በኩርና ጀግናው ኢየሱስ በሦስተኛው ቀን ከሞት ተነሣ፡፡ አሜን፡፡

የትንሣው ተጨባጭ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች

1. የተሰበረው የሮም መንግሥት ማህተም፡፡

2. እስከ ዛሬ አፉን ከፍቶ በየዓመቱ በሚሊዮኖች እየተጎበኘ ለእስራኤል መንግሥት ዋና የገብ ምንጭ እየሆነ ያለ ባዶ መቃብር/ ዛሬ ኢየሩሳሌም ሄዶ ማየት ይቻላል/፡፡ በዓለም ላይ ከተነሡ የሃይማኖት መሪዎች አንዱም የተነሣ የለም፡፡ መቃብሮቻቸው በተለያየ አገሮች እንዳሉ ናቸው፡፡

3. በሕግ የተቀመጠው ድንጋይ በመለኮት ኃይል መከባለል፡፡

4. የሮም ወታደሮች የነበሩና የኢየሱስ መቃብር ጠባቂዎች ብርቱ ድንጋጤ፣ ውድቀትና ሽሽት፡፡

5. አስከሬኑ የተጠቀለለበት ጨርቅ በመቃብር ውስጥ መገኘት፡፡

6. ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለሐዋርያት ደጋግሞ መገለጥ፣ ከዚያም ለ500 ሰዎች መታየትና በግልጽዳ አባቱ ማረግ፤

7. የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መነሳቱን ከተለያዩ የዓይን ምስክሮች የሰሙትን ብቻ ሳይሆን በዓይኖቻቸው ያዩትን በጥንቃቄ ጽፈው ለእኛ ማስተላለፋቸውና ተጨባጭ መረጃዎች በእጃችን መኖሩ፡፡ በዚህም ላይ የርቫርድ ዩኒቨርሲቲ አንድ ዓለማችን ዕውቅ የሕግ ፕሮፌሰር መረጃዎቹን በሳይንሳዊ መንገድ በጥልቀት ካጠኑ በኋላ፡- "እምነታችን የተመሠረተው በጠንካራ እውነት ላይ ነው፡፡ እውነቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት፣ አገልግሎት፣ ሞትና ትንሣኤ መሆኑና ይህም በዚያ ዘመን በነበሩ በዓይን ምስክሮች ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸው እርግጠኛ በሆኑ ጸሐፊውች የተጻፈ ከበቂ በላይ ማስረጃ መሆን የሚችል ዳጎስ ያለ መረጃዎች በእጃችን መኖራቸው ነው" ብለዋል፡፡

8. ከሞቱ በፊት ጥለውት የፈረጠጡ፣ እርሱ ሲያዝ ከእርሱ ጋር ለመታየት ፈጽሞ ያልፈቀዱና በአደባባይ የካዱት ተከታዮቹ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋለ በንስሐ ወደ እርሱ ተመልሰው፣ ለዓለም ሁሉ ያዩትን በድፍረትና በእምነት እየመሰከሩ በየተራቸው እርሱ ለእነርሱ ሰማዕት እንደሆነ እነርሱም ለእርሱ ሰማዕት በመሆን ወደ ቀጣዩ ሕይወት በድል መሻገር፡፡ ምናለባት ለውሸት አንድ ሁለት ምናልባት ይሞቱ ይሆናል፡፡ 12ቱም የእርሱ ሐዋርት በትልቅ ደስታና መሰጠት ለእርሱ ሰማዕት መሆን በትንሣኤው ብቻ ሳይሆን ለትንሣያቸውም ያላቸውን እርግጠኝነት ያመለክታል፡፡ ኢየሱስ ካልተነሣ ከመሞቱ በፊት ጥለውት የሸሹ እነዚህ ፊሪ የነበሩ ሰዎች ተመልሰው ትንሣኤውን በታላቅ ኃይል እየሰበኩ፣ እየኖሩ፣ እየጻፉ፣ እንዴት በተራቸው ለእርሱ ይሞታሉ?

9. በስሙ ዛሬም አጋንንትት ከሰዎች ይወጣሉ፤ ድውያንን ይፈወሳሉ፣ ሙታኖች ይነሳሉ ... ፡፡ ይህ የትንሣኤው አንዱ ማስረጃ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ በየትኛውም የሃይማኖት መሪ ስም ሞተው ተቀብረው ቀርቶ በሕይወትም እያሉ በስማቸው አጋንንትን ከሰዎች ማስወጣትና መፈወስ አልተቻለም፡፡ የትንሣኤ ንጉሥ በሆነው በኢየሱስ ስም ግን ተችሎዋል፡፡ ይህም የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ አንዱ ሕያው ማረጋገጫ ነው፡፡

10. ሌላው ጠንካራ ማስረጃ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ሕይወት በትንሣኤው ኃይል መለወጥና ለዘላለም መዳን፡፡ ዛሬ ከ2 ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ይህን የትንሣኤ ጀግና ይከተሉታል፣ ያመልኩታል፣ ይገዙለታል፣ ይሰብኩታል፣ ይኖሩለታል አንተስ/አንቺስ? ያለ እርሰ ድነት፣ ሕይወት፣ ሰላምና ዕረፍት የለም!

አሜን

መልካም የትንሣኤ ኑሮ
ክብር ለታረደው በግ፤ ሞትን ድል አድርጎ ለተነሳውና በትንሣኤው ኃይል እያኖረን ላለው፡፡ አሜን።

ትንሣኤው ለዘላለም የምንኖረው ሕይወት እንጂ በዓመት አንድ ቀን የሚከበር በዓል አይደለም።

የትንሣኤው ምስክር ጸጋአብ ነኝ፡፡
@nazrawi_tube