Get Mystery Box with random crypto!

ቻርለስ ፊኔ (Divine Encounter) “ከብዙ የጸሎት ትግል በኋላ አንድ ምሽት ‘ለእግዚአብ | ናዝራዊ Tube

ቻርለስ ፊኔ
(Divine Encounter)

“ከብዙ የጸሎት ትግል በኋላ አንድ ምሽት ‘ለእግዚአብሔር ነፍሴን በሚገባ ማፍሰስ አለብኝ’ የሚል ሐሳብ በውስጤ ፈሰሰ። የነፍሴ ለጸሎት መነሣቷ እጅግ አስደስቶኝ ነበርና ወደ ቢሮዬ ሄጄ መጸለይ ጀመርሁ።

“ክፍሉ ውስጥ እሳት አልነበረም፣ ብርሃንም አልነበረም። ነገር ግን ክፍሉ በብርሃን እንደ ተሞላ ይሰማኝ ነበር። የክፍሉን በር ለመዝጋት ተነሥቼ እየተመለስሁ ሳለሁ፣ ጌታ ኢየሱስን ፊት ለፊት በአካል ያየሁት መሰለኝ።

“ነገሩ የሚታየኝ በአእምሮዬ ነበር (mental state)። ልክ አንድን ሰው በአካል እንደማየው ነበር ማየቴን እያየሁት የነበረው። እርሱ ምንም አላለኝም። እጅግ አትኩሮ ያየኝ ነበርና ልቤ እጅግ ቀለጠ፤ ከዚያም በእግሩ ሥር ተደፋሁ። ነፍሴን አንድም ሳይቀር በፊቱ አፈሰስሁ፤ እንደ ሕፃን ልጅ ነበር ያለቀስሁት። በእንባ እግሮቹን እያራስኳቸው እንደ ነበር ነው የተሰማኝ።

“ለረጅም ጊዜ ተመስጦ ውስጥ ነበርሁና ነቅቼ ከቢሮ ውጭ አቀጣጥዬው የነበርኩትን እሳት ሳየው፣ የጨመርኩትን ማገዶ ሙሉ በሙሉ በልቶታል። እሳቱ ጋ መቀመጫ ወስጄ ልክ እንደ ተቀመጥሁ፣ በመንፈስ ቅዱስ ተጠመቅሁ። የመንፈስ ቅዱስ እሳት ውስጤን አጋየው።

“ልክ እንደሚነዝር ኤሌክትሪክ ነበር መንፈስ ቅዱስ ወደ ውስጤ ዘልቆ የገባው። የገጠመኝ ሰማያዊ ጉብኝት ልቤን በፍቅር አቀለጠው። በውስጤ የፈሰሰውን ፍቅር፣ ደስታና ሰላም ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል። የጌታ ፍቅር ልቤን በኀይል አሟምቶት ነበርና ጮክ ብዬ አለቀስሁ።

“መለኮታዊ ሞገዱ ደጋግሞ ደጋግሞ በላዬ ላይ ይዥጎደጎድ ስለ ነበርና ‘ይህ ሞገድ ከቀጠለ ወዮልኝ እሞታለሁ’ አልሁ። ነገር ግን ምንም የሞት ፍርሃት አልነበረኝም። በዚህ ሁኔታ ለምን ያህል ጊዜ እንደ ቆየሁ አላስታውስም።

“የነበርሁበት ክፍል ውስጥ የመዘምራን ቡድናችን መሪ የሆነ ባልደረባዬ ሲመጣ፣ በኀይል እየጮኽኩና ስቅስቅ ብዬ እያነባሁ ነበር ያገኘኝ። እርሱም ‘አቶ ፊኔ አሞሃል ወይ?’ አለኝ። ነገር ግን ልመልስለት አልቻልሁም። እርሱም ከቀድሞው ድምፁን ጨመር አድርጐ ‘ሕመም ይሰማሃል ወይ?’ ብሎ ጠየቀኝ። እኔም እንደ ምንም ኀይሌን አሰባስቤ ‘አይደለም እጅግ ደስተኛ ነኝ። ነገር ግን መኖር አልችልም’ አልኩት።”

@nazrawi_tube