Get Mystery Box with random crypto!

የጎጃም ኮማንድፖስት ባደረገው ክትትል የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ እያገኙ መሆኑን የአዊ ብሄረሰብ አስ | Natnael Mekonnen

የጎጃም ኮማንድፖስት ባደረገው ክትትል የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ እያገኙ መሆኑን የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር አርሶ አደሮች ተናገሩ።

ኮሩ በተሰማራበት ዞን ስር የሚገኙ ቲሊሊ ፣ እንጂባራ ፣ አዲስ ቅዳም ፣ ዳንግላ እና ሌሎች ወረዳዎች ስርጭቱ በተገቢው መንገድ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

አርሶ አደሮቹ በሰጡት አስተያየት ፣ የዘንድሮ የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት ስርጭት አምና ከነበረው አንፃር ስንመለከት ዋጋው ተመጣጣኝ ሲሆን ወቅቱን ጠብቆ በመምጣቱ ለስራችን ምቹ ሆኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ሰራዊቱ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እያደረገልን ሁሉም አርሶ አደር ድርሻውን በአግባቡ እየወሰደ ይገኛል ያሉት አርሶ አደሮቹ ፣ የጥፋት ቡድኑ የማዳበሪያ ግብዓቱን እንዳንወስድ በርካታ የሀሰት ወሬዎችን ቢነዛም አልተቀበልነውም ብለዋል፡፡

ከመንግስት ገንዘብ ከፍላችሁ አትውሰዱ እኛ በነፃ እንመጣለን ፣ በቅርቡ የማዳበሪያ ፋብሪካ እንገነባለን እያለ የበሬ ወለደ ወሬዎችን ቢያናፍስም አርሶ አደሩ ሀሰት መሆኑን ተገንዝቦ የቀረበለትን ማዳበሪያ ተገቢውን ክፍያ ለመንግስት በመክፈል እየወሰደ እንደሚገኝ አረጋገጠዋል ፡፡

የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል መንገሻ ሞላ ፣ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭቱ ለአርሶ አደሩ አማካኝ በሆኑ ቦታዎች ላይ እንዲከማች በማድረግ እየተሰራጨ እንደሚገኝ እና ሰራዊቱ ግብዓቱን አጅቦ በማምጣት የእደላ ስራውን በቅርበትና በትኩረት እየተከታተለ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ሰራዊቱ ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የተወጣጣ የህዝብ ልጅ በመሆኑ ማንኛውም ፈተና ሳይበግረው ለህዝባችን ሰላምና ልማት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ግዳጁ የሚጠይቀውን ሁሉ ዋጋ በመክፈል የህዝባችንን ሰላምና ልማት የማረጋገጥ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎሬል መንገሻ ሞላ አረጋግጠዋል፡፡