Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው 4 ሳምንታዊ በረራዎችን ማድረግ ሊጀምር መ | Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው 4 ሳምንታዊ በረራዎችን ማድረግ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

ዋርሶው በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) የተመዘገቡ ቅርሶች መገኛ፣ የድንቅ ኪነ ሕንፃዎች ማዕከል እና ታሪክንና ዘመናዊነትን አጣምራ የያዘች በዓለም በቱሪስት መዳረሻነታቸው ከሚጠቀሱ ቀዳሚ ከተሞች አንዷ ነች። አየር መንገዱ ወደ እዚህች ከተማ ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ 4 ሳምንታዊ በረራዎችን ማድረግ ሊጀምር መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡
አየር መንገዱ የበረራ ትኬት ለማግኘት ለሚፈልጉ ደንበኞቹ በአየር መንገዱ ተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ፣ ድረ ገጽ ወይም በትኬት ሽያጭ ቢሮዎች በመቁረጥ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡