Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘አስተውሎት’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም አስ | Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘አስተውሎት’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም አስመረቀ፡፡

ፊልሙ ትኩረቱን ኢንስቲትዩቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ባከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ አድርጓል፡፡

ፊልሙን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሰውኛ ፕሮዳክሽን እና ኢንተርቴይንመንት ጋር በመሆን በጋራ አዘጋጅተውታል።

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዝግጅቱም ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢንጅነር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና እሳቤው “በትልቅ እናስባለን፤ ከትንሹ እንጀምራለን” በሚል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዛሬ ላይ ሀገራችን ከዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆን ሀገር የሚያኮራ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።