Get Mystery Box with random crypto!

በአሸባሪው ሸኔ ታግተው የነበሩ 4 ሲኖትራክ ገልባጭ መኪናዎችን ከነ ሹፌሮቻቸው ማሥመለስ ተችሏል። | Natnael Mekonnen

በአሸባሪው ሸኔ ታግተው የነበሩ 4 ሲኖትራክ ገልባጭ መኪናዎችን ከነ ሹፌሮቻቸው ማሥመለስ ተችሏል።

የደቡብ ዕዝ ክፍለ ጦር በአርሲ ዞን ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ መጃ ሸነን ቀበሌ ፈርዳ አካባቢ በሸኔ የሽብር ቡድን ታግተው የነበሩ አራት ሲኖትራክ ገልባጭ ተሽከርካሪዎችን ከነሹፌሮቻቸው ከእገታ አስለቅቋል።

ከማህበረሰቡ የተገለለው እና በተደጋጋሚ በሁሉም አካባቢዎች ከባድ ምት እያረፈበት የሚገኝው ዘራፊውና አሸባሪው ቡድን ንብረት በማገት በገንዘብ መደራደር እንደ ዋነኛ አማራጭ አድርጎ ቢንቀሳቀስም በመከላከያ ሠራዊቱ እና በፀጥታ ሃይሉ ጥምረት እየተመታ የዘረፈው ንብረትም እየተመለሰ መሆኑን በቀጠናው የሚገኘው ክፍለጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሳሊወን ክብረሃሰን ገልፀዋል።

የታገቱት ሹፌሮችም ሸኔ ብር ካልስገባችሁ እንገላችኋለን በማለት ሲዝቱብን ሠራዊቱ ደርሶ በከፈተው ተኩስ ሸኔዎቹ እየጮሁ ሲሮጡ እና ሲመቱ እኛ በሠላም ከነ ንብረታችን ከሠራዊቱ ተቀላቅለናል ብለዋል።