Get Mystery Box with random crypto!

በኤርትራ ታስረው የነበሩ 46 የትግራይ ክልል ተወላጆች ተለቀቁ Good News : ለሁለት ዓመታት | Natnael Mekonnen

በኤርትራ ታስረው የነበሩ 46 የትግራይ ክልል ተወላጆች ተለቀቁ

Good News : ለሁለት ዓመታት በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ወቅት፤ ወደ ኤርትራ ተወስደው ታስረው ከነበሩ የክልሉ ተወላጆች ውስጥ አርባ ስድስቱ በትናትናው ዕለት ተለቀቁ። እስረኞቹ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 4፤ 2016 ጠዋት ሽራሮ ከተማ መግባታቸውን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ ሙሉ ብርሃነ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።

እስረኞቹ በጦርነቱ ጊዜያት ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በኤርትራ ሰራዊት ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ፤ በኤርትራ የጋሽ ባርካ ዞን መቀመጫ በሆነችው የባረንቱ ከተማ ታስረው የቆዩ መሆናቸውን አቶ ሙሉ ገልጸዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በተመለከተችው የተፈቺዎች ዝርዝር፤ የአብዛኞቹ መኖሪያ አድራሻ በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ውስጥ ባሉ አካባቢዎች የሚገኝ ነው።

ከኤርትራ ጋር በሚዋሰነው በዚህ ዞን ስር ከሚገኙ አካባቢዎች ውስጥ በርካታ ነዋሪዎቿ የተወሰዱባት የሽራሮ ከተማ ትገኝበታለች። እስረኞቹ ዛሬ ጠዋት በ”አይሱዙ” ተሽከርካሪ ተጭነው ሽራሮ ሲደርሱ፤ የከተማይቱን ከንቲባ ጨምሮ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜን ምዕራብ ዞን አስተዳደር አመራሮች እና የጸጥታ አካላት አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብበዋል።