Get Mystery Box with random crypto!

ክፍለጦሮች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው መቀጠላቸው ተገለፀ። በምስ | Natnael Mekonnen

ክፍለጦሮች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው መቀጠላቸው ተገለፀ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በዲጋ ወረዳ የማዕከላዊ ዕዝ አንድ ክፍለጦር በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ላይ ሰሞኑን ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሸን የሸኔ ቡድን መደምሰሱን የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ እንዳለው ገልፀዋል።

የህዝብን ሠላም መንሳት አላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለማስቆምና ቡድኑን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት የሃገሩን ሰላም ለማረጋገጥ ክፍለጦሩ ተልዕኮውን በድል አድራጊነት ቀጥሏል ሲሉ አዛዡ ተናግረዋል።

ክፍለጦሩ ሰሞኑን በጠላት ላይ በወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ለጥፋት ተግባሩ ይጠቀምበት የነበረውን  ብሬን ፣ ክላሽ ፣ የክላሽ መጋዘን ፣የብሬን ጥይት ፣ ቦንብ፣ የክላሽ ጥይት ፣ሽጉጥና የተለያዩ መድሃኒቶችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ እንዳለው አሳውቀዋል።

በተመሳሳይ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሀባቦ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ህብረተሰቡን ለስቃይ እና ለእንግልት ሲዳርግ እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ሲዘርፍ እና ሲያቃጥል የቆየዉ አሸባሪዉ የሸኔ ቡድን ክፍለ ጦሩ በሚወስደው የተቀናጀ እርምጃ እጅ እየሠጠ ይገኛል።

እጃቸውን ለሰራዊቱ  ከሰጡት መካከል ለሊሳ ዋሚ ላለፉት አመታት በሽብር ቡድኑ በቆየሁበት ጊዜ ህብረተሰቡን በማሠቃየት በዘረፋ ላይ ተሰማርቸ ነበር ግን ትክክል አልነበርኩም አሁን ወደ ሠላም ተመልሻለሁ ብሏል።

የአካባቢዉ ነዋሪዎች የሽብር ቡድኑ አባላት በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሰራዊቱ እጅ መስጠታቸውን እንዲቀጥሉበትና በአካባቢውም የልማት ሥራ እንዲሠራ ሃሳብ ሰጥተዋል።