Get Mystery Box with random crypto!

በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ! ላለፉት ሦስት ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረ | Natnael Mekonnen

በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ!

ላለፉት ሦስት ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ ከጥር  21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ወራት ታግዶ የቆየው የመሬት አገልግሎት፣ የዜጎችን መብት የጣሰ እንደነበር በመናገር  ተገልጋዮች ሲያማርሩ ቆይተዋል።

አስተዳደሩ እንደገለጸው አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከቀን ከመጋቢት 23 ቀን2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን አስታውቋል።