Get Mystery Box with random crypto!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ60 ሺህ መኖርያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክትን የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ የአ | Natnael Mekonnen

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ60 ሺህ መኖርያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክትን የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ60 ሺህ መኖርያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክትን የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገነባው እና "ኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ" የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ፕሮጀክቱ፤ ኦቪድ ግሩፕ በተሰኘ የግል ድርጅት የሚገነባ ነው።

ከንቲባ አዳነች የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ጥያቄ ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።

"ባለፉት ዓመታት ቃላችንን በተግባር ማሳየት ችለናል" ያሉት ከንቲባዋ "ዛሬም የገባነውን ቃል በተግባር አሳይተን እናረጋግጣለን" ሲሉ ገልጸዋል።

በ565 ሄክታር ላይ የሚያርፈው የመኖርያ ቤት ግንባታው፤ ከ 300 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ያሉት ደግሞ የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ ናቸው።

ፕሮጀክቱ የመኖርያ ቤት ልማት ብቻ ሳይሆን አዲስ ከተማ የመገንባት ሂደት ጭምር በመሆኑ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።