Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባ | Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባካሄደው ኦፕሬሽን ሰላማዊ ሰዎችን በመግደልና በማገት የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ በርካታ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላትን ደመሰሰ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባካሄደው ኦፕሬሽን ሰላማዊ ሰዎችን በመግደልና በማገት የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ በርካታ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላትን ደመሰሰ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ልዩ ቦታው ቦፋ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በየመንገዱ ተሽከርካሪዎችን እያስቆሙ በመዝረፍ፣ ሰላማዊ ሰዎችን በማገትና በመግደል የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ በርካታ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላትን ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ደምስሶ በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላትንም መቆጣጠሩን የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

የሸኔ የሽብር ቡድን ለእኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ይጠቀምባቸው የነበሩትን የጦር መሣሪያዎች እና ጀነሬተሮችን እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች በተካሂደው ኦፕሬሽን መያዛቸውንም መምሪያው አስታውቋል።

የሸኔ የሽብር ቡድን የሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎችን ከሽብር ቡድኑ በማፅዳት የሕዝብን ሰላም ለማረጋገጥ እየተካሄደ ያለው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀው የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ መምሪያው ኅብረተሰቡ የሽብር ቡድኑን አባላትና ሴሎቻቸውን አጋልጦ ለፀጥታ አካላት አሳልፎ እየሰጠ ያለውን ተግባር የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።