Get Mystery Box with random crypto!

#የአፋሩ ወጣት አመራር አቶ መሀመድ ሰሠን በአመራር ብቃቱና በስነምግባሩ ጭምር በአፋር ህዝብ ዘንድ | Natnael Mekonnen

#የአፋሩ ወጣት አመራር አቶ መሀመድ ሰሠን በአመራር ብቃቱና በስነምግባሩ ጭምር በአፋር ህዝብ ዘንድ የተወደደ ቀጣይም ክልሉን ይለውጣሉ ይመራሉ ተብሎ ተስፋ ከተጣለባቸው ወጣት አመራሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት በአፋር ህዝብ ዘንድ የተወደደና የተመረጠ ወጣት አመራር ነው፡፡

አቶ መሀመድ ሀሠን በአፋር ክልል ለውጡን ተከትሎ ወደ ከፍተኛ አመራርነት ከመጡ ወጣት አመራሮች መካከል ቀዳሚው ወጣት አመራር ነው::በለውጡ ማግስት የዛሬ 3አመት በአፋር ክልል የድርጅቱ አብዴፓ ባደረገው የድርጅቱ ጉባኤ ላይ ለመጀመሪያ ግዜ የጉባኤተኛውን ሙሉ ድምፅ በማግኘት ወደ ማእከላዊ ኮሚቴ የገባ ብቸኛው አመራር የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰአትም መሀመድ ሀሰን ክልሉን በታማኝነት እያገለገለ ያለ ወጣት አመራር ነው ፡፡

ከአመት በፊት በተደረገው በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በብልፅግና የዱብቲ ወረዳ የክልል ምክር ቤት የብልፅግና እጩ ተወዳዳሪ በመሆን በቀረበበትም በዱብቲ ወረዳ በምርጫው በሙሉ ድምፅ(75.685)ድምፅ በማግኘት በአንደኝነት ማሸነፉን ምርጫ ቦርድ አስታውቆል ወጣቱ መሀመድ ሀሰን የአፋር ህዝብ በሙሉ ድምፅ የመረጠው እሱ ባለው አቅምና በአመራርነት በሰራው ስራዎች በህዝቡ ዘንድ ሁሌም ተመራጪና ተወዳጅ አመራር አድርጎታል፡፡

በቅርቡም በተደረገው የብልፅግና ማእከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ላይ በጉባኤ ከተሳተፉ 1445 ሰዎች 817 ድምፅ በማግኘት በ12ኛ ደረጃ የተመረጠ ወጣት የሀገራችን ብልፅግና ተስፋ ከተጣለባቸው ወጣት ተተኪ አመራሮች ግንባር ቀደም መሆኑን በጉባኤው ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ያስመሰከረ ምርጥ ተተኪ ወጣት አመራር መሆኑን ያሳያል፡፡