Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ወለጋ ሄደዋል። በምስራቅ ወለጋ ከሚገኙ የማህበረሰብ | Natnael Mekonnen



የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ወለጋ ሄደዋል። በምስራቅ ወለጋ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር መወያየታቸውም ተገለጿል። በንጹሃን ግድያ፡ መፈናቀልና ዘረፋ በጸጥታ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው የምስራቅ ወለጋ ዞን ያመሩት አቶ ሽመልስ ውይይቱን ያካሄዱት በነቀምት ከተማ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ሕዝቡ በፀጥታ ችግር ለመፈናቀል፣ ለንብረት ዘረፋ እና ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች መጋለጡን የውይይቱ ተሳታፊዎች አንሥተዋል ሲል የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አመልክቷል። ከለፈው ሳምንት ወዲ ሽእንደአዲስ ባገረሸው ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በተለይ በኪራሙ ወረዳ ማንነትን መሰረት ባደረገ ጥቃት ክ60ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የአቶ ሽመልስ አብዲስ ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን ማቅናትን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የኪራሙ ወራዳ ተፈናቃይ ከችግሩ ሰለባዎች ጋር ሳይገናኙ ችግር ፈጣሪዎችን አወያይተው መመለሳቸው የሚያመጣው ለውጥ የለም ይላሉ።