Get Mystery Box with random crypto!

ሕወሓት ሰላማዊ ዜጎችን እያሰረ መሆኑ ተገለጸ አሸባሪው ሕወሓት አስገድዶ ወደ ግዳጅ ያስገባቸው ም | Natnael Mekonnen

ሕወሓት ሰላማዊ ዜጎችን እያሰረ መሆኑ ተገለጸ

አሸባሪው ሕወሓት አስገድዶ ወደ ግዳጅ ያስገባቸው ምልምሎች መካከል ለመሸሽ የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ዘመዶቻቸው የታሰሩባቸው ሦስት ሴቶች ገለፁ።

አሸባሪው ሕወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎችን ያሳተፈ ቅስቀሳ በማድረግ ለጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ናቸው፡፡

ሱዳንስ ፖስት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሦስት የትግራይ ተወላጆች በኢሜይል መልዕክት አድርሰውኛል ብሎ እንደዘገበው ሕወሓት የሚያደርገው ጦርነት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ጋር ብቻ ሳይሆን የክልሉን ሰላማዊ ዜጎች በማሰር ትርጉም የለሽ ተግባር እየከወነ ነው፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እና ሰላማዊ ዜጎች የሕወሓትን የሽብር ተግባር ለመቀላቀል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሲታሰሩ ይህ የመጀመሪያ አይደለም ያሉት ነዋሪዎቹ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ሕወሓት ጦርነት እንዳይቀጥልና ሰላምን እንዲቀበል ጫና ማድረግ እንደሚጠበቅበት ጠይቀዋል፡፡