Get Mystery Box with random crypto!

MILLENNIUM KOMBOLCHA PREPARATORY SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ nadewass — MILLENNIUM KOMBOLCHA PREPARATORY SCHOOL M
የቴሌግራም ቻናል አርማ nadewass — MILLENNIUM KOMBOLCHA PREPARATORY SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @nadewass
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

QUALITY EDUCATION FOR ALL

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-05 19:17:32 የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሙሉ ስኮላርሺፕ መሰጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡
የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና በተሰጠበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸው፥ "ለተማሪዎቹ እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡
ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
"ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ በተለይም ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁ ብለዋል።
"በትውልዶች ግንባታ ላይ ነው፤ ያለፈው ትውልድ አልፏል አሁን ያለው ትውልድም አነሰም በዛም ለሀገሩ እየለፋ ነው፤ እናንተ ግን ገና ከምንጩ ለሀገራችሁ የምትጠቅሙ እንድትሆኑ ከሰፈራችሁ ወጣ ብላችሁ ለሀገር እንድታስቡና ቀድሞ የነበሩ ስመጥር ኢትዮጵያውያን ምሁራን ከእናንተ ውስጥም እንዲወጡ አደራ እንላችኋለን" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው፥ "እንደ መንግስትና ትምህርት ሚኒስቴር የተጀመረው ለውጥ የፈተናዎችን ቅቡልነት በማረጋገጥ ቢሆንም በሁሉም መስኮች የሚስተዋሉ የትምህርት ስብራቶችን መጠገንና በሁሉም መመዘኛ ብቁ የሆኑ ተማሪዎችንና ጠንካራ ዜጎችን ለመፍጠር እንተጋለን" ብለዋል፡፡
በዚህ የለውጥ ሂደት ደግሞ ተጠቃሚውም ተጎጂውም ህብረተሰቡ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ በቀጣይም ብቁ ተማሪዎችን የመፍጠሩ ሂደትና የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
እውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስክ ከ700 ድምር ውጤት ከ600 በላይ ያመጡ 263 ተማሪዎች እና በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ከ600 ድምር ውጤት ከ500 በላይ ያመጡ 10 ተማሪዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ለሁሉም ተማሪዎችም ላፕቶፕ በሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ via Fana
429 views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 19:10:04 "ብሔራዊ እና ክልላዊ ፈተናዎችን የሚወስዱ ተፈታኞች የረፍት ጊዜያቸውን ለክለሳ ጥናት ሊያውሉ ይገባል" ዳዊት አስራት (ዶ.ር)
ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ መሰናዶ የሚገኙ ተማሪዎች የመጀመሪያውን ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና አጠናቅቀዋል። የሁለተኛው ወሰነ ትምህርት እስኪጀመር በሚኖራቸው ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይቆያሉ። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ዘመድ መጠየቅ፣ ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት፣ የፈተና ውጤትን ገምግሞ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን የበለጠ ማጥናት፤ ወደ መዝናኛ ቦታዎች መኼድ እና የመሳሰሉ ተግባራትን ያከናውናሉ።
በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርትና ሥነ ባሕሪ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር ዳዊት አስራት (ዶ.ር) በተለይም ብሄራዊ እና ክልላዊ ፈተናዎችን የሚወስዱ ተማሪዎች የረፍት ጊዜያቸውን በዝግጅት ማሳለፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል። በማጠቃለያ ፈተናዎች ላይ ተፈትነው ያልመለሷቸውን ጥያቄዎች የበለጠ ጥናት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ አውቀው ማለፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
እንደ ዶክተር ዳዊት ገለጻ ተማሪዎች በረፍት ጊዜያቸውም ቢኾን ሙሉ በሙሉ ከጥናት ውጭ መኾን የለባቸውም። ከመዝናናት ጎን ለጎን ያለፈውን የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት የሚከልስ እና መጭውን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርትም ቀድሞ የሚዳሰስ ጥናት ማካሄድ ለጥሩ ውጤት እንደሚያበቃ ገልጸዋል። በዚህ የረፍት ጊዜ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከጥናት ከራቁ የዕውቀት ትስስሩ ይቋረጥና ውጤታማነትን ይቀንሳልም ብለዋል።
ዶክተር ዳዊት በተለይም የብሔራዊ እና ክልላዊ ፈተናዎችን ለመውሰድ የሚዘጋጁ ተማሪዎች የረፍት ጊዜያቸውን ለክለሳ ጥናት ሊያውሉ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። በሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ፈተናዎች ላይ ውጤታማ ለመኾን ይህን የረፍት ጊዜ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ነው ያሉት።
ፈተና ሲደርስ ሳይኾን ቀደም ብሎ የትምህርት አይነቶችን በተገቢው ስብጥር የጥናት ሽፋን መስጠት ለጥሩ የሥነ ልቦና ዝግጅት እንደሚያበቃም ዶክተር ዳዊት አመላክተዋል። አንድን የትምህርት አይነት ለረጅም ጊዜ ከማጥናት ይልቅ ሁሉንም የትምሕርት አይነቶች እያፈራረቁ እና በየመካከሉ ረፍት እየወሰዱ ማጥናት እንደሚገባ አብራርተዋል። ይኽ ዘዴ ኹሉንም የትምህርት አይነቶች ለመሸፈን ከማገዙም በተጨማሪ የመሰልቸት ባሕሪን ያስወግዳል።
ዶክተር ዳዊት በዚህ የረፍት ጊዜ ተማሪዎች ያለፏቸውን ክፍሎች መጻሕፍት እንደገና በመከለስ በርካታ ጥያቄዎችን እያወጡ መልስም በመስጠት ራሳቸውን መፈተን እንዳለባቸው ተናግረዋል። ራሳቸው የሚያወጧቸው ጥያቄዎች በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይም የሚመጡበት አጋጣሚ ይኖራልም ብለዋል። ይኽም ለበለጠ ዝግጁነት እና ለጥሩ ውጤት እንደሚያበቃ ገልጸዋል።
ተማሪዎች በሚያጠኑበት ጊዜ በጥልቅ መረዳት መኾን እንዳለበት ዶክተር ዳዊት ይመክራሉ። በተለይም ለብሔራዊ ፈተና የሚዘጋጁ ተማሪዎች የቀረው ጊዜ አጭር መኾኑን አውቀው ከወዲኹ ጥልቅ ጥናት መጀመር እንዳለባቸውም ገልጸዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፈተና ለመዘጋጀት ታስቦ የሚደረገው ግልብ የኾነ ጥናት ወይም "ሽምደዳ" ለተማሪዎች ዘላቂ ዕውቀት እንደማይጠቅም አመላክተዋል።
አሚኮ
410 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 18:43:43 ለሚሊኒየም ከ /ቻ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2014ዓ.ም ለሪሚዲያል ኮርስ (ድጋፍ) ወደ ዩኒቨርስቲዎች ለምትገቡ ተማሪዎች በሙሉ
እስከ አርብ (10 / 06/ 2 015 ብቻ ት /ቤት
በመገኘት የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን እንድትሞሉ ት/ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል ::
Natural ለወንድ 263
ለሴት 227
social ለወንድ 220
ለሴት 190 ነው።
995 views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 18:37:32 # ማስታወቂያ

በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-

በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ) ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ

https://student.ethernet.edu.et

በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
816 views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 19:14:55 ማስታዎቂያ
የ20014 ተፈታኝ እና ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ በ 9/6/15 በትም/ቤት በመገኘት የዮኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን
866 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 19:06:30
#MoE

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን አማካይነት እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

   ---ETHIO-MEREJA--
   T.me/ethio_mereja
851 views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 09:08:18 # ማስታወቂያ

በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-

በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ  መሆኑን እንገልጻለን።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ)  ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን  በቀጣዩ ሊንክ 

https://student.ethernet.edu.et

በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

                         ትምህርት ሚኒስቴር!
1.0K views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 09:07:10 ለ12ኛ ክፍል 2014 ተፈታኞች
አዳማ እና አ/ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ያለ ውድድር መመደብ የምትፈልጉ ዛሬ እስከ 12 ሰዓት ድረስ ጋሼ አሊ Ict መምህር ኮንታክት በማድረግ አዳማና አ/አበባ ን እንዴ ምርጫችሁ 1ኛ እና 2ኛ በማድረግ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
Nadew Assefa
874 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 21:53:43 ለሚሊኒየም 2 ኛ ደረጃ ት /ቤት ተማሪዎች
በውሎ ዩኒቨርስቲ ኮምፒውተር ስልጠና
ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ከየካቲት 11 - 13
መሆኑን እንገልፃለን።
1.4K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 19:23:59 ለሚሊኒየም 2ኛ ደረጃ የ2014ዓ.ም 12 ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች
የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን ማስተካከል ለምትፈልጉ ተማሪዎች አርብ ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ብቻ ት/ቤት ግቢ በመገኘት እንዲታስተካክሉ በጥብቅ እናሳስባለን :: ለሌሎች ጓደኛዎቻችሁ ኢንፎርሜሽን ተለዋወጡ !!
1.3K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ