Get Mystery Box with random crypto!

Esdros S.C

የቴሌግራም ቻናል አርማ esdrossc — Esdros S.C E
የቴሌግራም ቻናል አርማ esdrossc — Esdros S.C
የሰርጥ አድራሻ: @esdrossc
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.50K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ/ማህበር የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ፡፡
This is Esdros S.C's official Telegram channel.
For more updates please visit www.Esdros.com

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 16:11:31
589 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 16:09:13 የአቡነ ጎርጎርዮስ ተማሪዎች እና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የእረፍት ጊዜ
**********
ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን ያላቸውን ተሰጥኦ በማዳበር እና የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን በመስራት ያሳልፋሉ፡፡ በአቡነ ጎርጎርዮስ የሚማሩ ተማሪዎችም የተለያዩ ልምምዶችን በማድረግ የእረፍት ጊዜያቸውን በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
በቃሊቲ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የክረምት ጊዜያቸውን የአብነት ትምህርት በመማር እና የተለያዩ ተሰጥዋቸውን በማዳበር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች በምን መልኩ ጊዜያቸውን እየተጠቀሙ እንደሚገኙ በዚህ መልኩ ተናግረዋል፡፡
ተማሪ ቢታኒያ መርእድ ክረምትን ተሰጥኦዎቼን በማዳበር፣ለቀጣይ ዓመት በመዘጋጀት እና እረፍት በማድረግ እያሳለፍኩ እገኛለሁ ብላለች፡፡ በዚህም የበገና ትምህርት እየተማረች እንደምትገኝ እንዲሁ የተማረችውን ትምህርት ለማዳበር የተለያዩ መጽሐፎችን በማንበብ እና የግዕዝ ሚስጢራዊ ቁጥሮችን ከተለያዩ የግእዝ መዛግብቶች ላይ በመውሰድ ትክክለኛ ፍቺያቸውን በመፈለግ በማጥናት ላይ እንተምትገኝ ገልጻለች፡፡
ተማሪዎቹ የሚፈልጉትን ትምህርት ከመማር ባሻገር እረፍታቸውን የተለያዩ ተሰጥዋቸውን ማዳበር በሚያስችላቸው ነገር ላይ ሲያሳልፉ ቆይተዋል፡፡ ተማሪ በሱፍቃድ ቢያዝን የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን የሥእል ችሎታ እንዳለው በመግለጽ የተለያዩ የሥዕል ማስተማሪያ ምስሎችን በማየት የሥእል ችሎታውን እያዳበረ እንደሚገኝ፣ ለቀጣይ ክፍል ትምህርቱን እያጠና እንዲሁም በገና እየተማረ እንደሆነ እና በቤት ውስጥም በገና በመደርደር እንደሚያሳልፍ ገልጾልናል፡፡ በዚህም እኔ የተፈጠርኩት እግዚአብሔርን ለማመስገን ስለሆነ በገናዬን ተጠቅሜ እግዚአብሔርን አመሰግንበታለሁ ብሏል፡፡ ስለዚህ ሌሎች ልጆችም በርትታችሁ ተሰጥዋችሁን ማዳበር ይጠበቅባችኋል ሲል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
መምህር ገብረእግዚአብሔር ውቤ በቃሊቲ አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት የግእዝ መምህር ሲሆኑ ልጆች የክረምት ጊዜያቸውን አልባሌ ነግሮች ላይ ከማሳለፍ ይልቅ ለእነርሱ ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ማሳለፍ እንዳለባቸው በማንሳት ተማሪዎች ጊዜያቸውን የተለያዩ ጠቃሚ ነገሮችን በማድረግ እያሳለፉ እንደሚገኙ እና እንዲሁም ያላቸውን ተሰጥኦ በማዳበር ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡
ናፍሌት ሙሉጌታ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ግጥም መግጠም በጣም እንደምትወድ በመጥቀስ የክረምት ጊዜዋንም ግጥሞችን በመጻፍ እንዳሳለፈች ገልጻልናለች፡፡ በአቅራቢዋ የሚገኙ ነገሮችን በማየት ጥሩ ከሆነ በጥሩ እንዲሁም መጥፎ ከሆነ ወደ ጥሩ እንዲለወጥ በግጥም ሀሳቦቿን እንደምትጽፍ ተናግራለች፡፡
ከትምህርቷ ጎን ለጎን ቅኔን አጥብቃ እንደያዘች በማንሳት ንግግሯን የጀመረችው የአብስራ ዋለ ስትሆን ከሚያስተምሩን አባቶች ባለኝ ትርፍ ጊዜ የግእዙን ቅኔ በመቀበል በቃሏ በመሸምደድ ትርጉሙን በመጠየቅ እና በማን እንደፈለሰፈ በማወቅ ብሎም እርቃቄ ለሰሙ እና ለወርቁ በመለየት እንደምታጠና ገልጻለች፡፡ በዚህም በዚህ ዓመት በተካሄደው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አውደርዕይ ላይ በዚህ ዘርፍ አሸናፊ እንደሆነች ጠቅሳለች፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች በክረምት መርሃ ግብር የአብነት ትምህርት እና የቀለም ትምህርትን በማስተማር ወደ ማጠቃለያው ላይ የደረሰ ሲሆን በዚህም ተማሪዎች ክረምቱን ተጠቅመው የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት፣ያላቸውን ተሰጥኦ በማዳበር፣ለቀጣይ ክፍል በመዘጋጀት እና ጥሩ የሚባል ጊዜን ከወላጆቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር በማሳለፍ እያጠናቀቁ ይገኛሉ፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ
622 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:57:09
767 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:56:01 በወልድያ አዲስ ለተከፈተው አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ሥልጠና ተሰጠ
*************
በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ አዲስ ለተከፈተው ወልድያ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ለሚገኙ አዲስ ርእሰ መምህር፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ”Induction and Socialization” በሚል ርዕስ ላይ በወልድያ ከተማ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ሥልጠናው በወልድያ በ2015ዓ.ም አዲስ ለተከፈተው የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ሥራ ለሚጀምሩ አዲስ መምህራን፣ ርዕሰ መምህር እና የአስተዳደር ሰራተኞች የተሰጠ ሲሆን የድርጅቱን እሴት፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና የአሰራር ባህል ማሳወቅ ብሎም የቅድመ ሥራ ሥልጠና እና የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ታሪካዊ ዳራ የሚሉት በሥልጠናው የተካተቱ ርዕሶች ናቸው፡፡
በመሆኑም የአክስዮን ማኅበሩ አደረጃጀት፣ እሴት፣ አላማ እና ተልዕኮ እንዲሁም የአሰራር ባህል በዝርዝር ቀርቧል፡፡ እንዲሁም የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሙያዊ ሥነ ምግባር ምን ይመስላል፣ የወላጅ አያያዝ እና የድርጅቱን ዕሴት ወደ ማህበረሰቡ እንዴት ማስረጽ እንደሚቻል በሥልጠናው በስፋት ተዳሷል፡፡
ሥልጠናው አዲስ አበባ የሚገኙ የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የአሰራር ሂደቶችን ፣ የተሰሩ በርካታ ተሞክሮዎችን እና ተግባራዊ ክንውኖችን በምስል እና ድምጽ በተደገፈ መልኩ በማሳየት ተግባራዊ ተሞክሮዎችን ማካፈል ያስቻለ ነው፡፡
የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የሆኑት ዲያቆን ፍቃደአብ ሙላው በሥልጠናው ያላቸውን አስተያየት ሲናገሩ ለአዲስ ቅርንጫፍ የሚያስፈልጉ ሥልጠናዎች በመሰጠታቸው በቀጣይ ለምንሰራቸው ሥራዎች መስፈንጠሪያ ሀሳብ እንደ ርዕሰ መምህር እንዳገኙ በማንሳት ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር እና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በኔነት ስሜት ለመስራት በቁርጠኝነት እንደተዘጋጁ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱን የተማሪ ወላጆች በመሰብሰብ ጊዚያዊ የወላጅ ኮሚቴ የተቋቋቀመ ሲሆን በዚህም የትምህርት ጥራት የወላጅ ኮሚቴ፣ የትራንስፖርት ወላጅ ኮሚቴ፣ የሥነ ምግባር ወላጅ ኮሚቴ እና ምቹ የትምህርት አካባቢን መፍጠር ላይ ያተኮሩ አራት ኮሚቴዎችን ማቋቋም ተችሏል፡፡ እንዲሁም በቀጣይ የሚሰሩ ሥራዎች ላይ ውይይት በማድረግ በቂ ግንዛቤ ማስረጽ ተችሏል፡፡
የተማሪ ወላጆችም ለአካባቢው ማህበረሰብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ቢሰራ እና ቀጣይነት ያላቸው ሥልጠናዎች ቢሰጡ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ ሥልጠናው ለአርባ አምስት ተሳታፊዎች ለሁለት ቀን የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞች በቆይታቸው የተቋሙን የስራ ባህል፣ ዕሴት፣ ራዕይ እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎትን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቂ ግንዛቤ መውሰድ የቻሉበት ነው፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ
787 views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:58:34
972 views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:52:19 አክስዮን ማኅበሩ ሥልጠና ሰጠ
*******
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለሥራ አመራሮች፣ ለርዕሰ መምህራን እና ለምክትል ርዕሰ መምህራን በኢትዮጵያ ሆቴል ሥልጠና ሰጠ፡፡
የአመለካካት ለውጥን ለማሳደግ እና የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥን የተሻለ ማድረግ ያስችል ዘንድ “Attitude Skills for Success at Work in Life” እና “ customer service in an organization” የደንበኞች አገልግሎት በድርጅት ውስጥ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተሰጥቷል፡፡
ሥልጠናው በ2015ዓ.ም ከተያዘ እቅድ መካከል ሲገኝ የአክስዮን ማኅበሩ የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ፣ ከኒው አፍሪካ ኮንሰልተንሲ ፈርም እና ከዳይሬክተሮች ቦርድ ጋር በመተባር ያዘጋጀው ሲሆን የሥልጠናው ዋና ግብ ተሳታፊዎቹ ተገቢ የሆነ የአመለካከት ዕውቀትን እና ክህሎትን እንዲጨብጡ በማድረግ በሥራቸው እና በአኗኗራቸው ዘይቤ ለውጥ እንዲያመጡ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
በተጨማሪም የድርጅቱን የአመራር ብቃት ይበልጥ ለማሳደግ ፣ የሰራተኞችን አመለካከት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ፣ በትምህርት ጥራት ፣ሥነ ምግባር እንዲሁም ውጤታማ የሥራ አፈጻጸም ለማምጣት ታስቦ ሥልጠናው ተሰጥቷል፡፡
በዕለቱ የአክስዮን ማኅበሩ የፋይናንስ እና አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አንተነህ ፈለቀ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የሥልጠናውን መርሃ ግብር ያስጀመሩ ሲሆን በንግግራቸውም ድርጅቱ በ2014ዓ.ም ለ642 ሰራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በ13 የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠናዎችን መስጠት እንደቻለ በመጥቀስ በተያዘው በ2015 በጀት ዓመትም የሰራተኛውን እና የሥራ ኃላፊዎችን አቅም ከማጎልበት አንጻር 22 ሥልጠናዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች 1200 ለሚሆኑ ሰራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች ለመስጠት እቅድ እንደተያዘ ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ የአመራር ብቃት በማሳደግ የደንበኞችን እርካታ ከፍ ለማድረግ ያግዝ ዘንድ ሥልጠናውን እንዳዘጋጀ የጠቀሱት አቶ አንተነህ ሰልጣኞች በሚኖራቸው ቆይታም በንቃት እንዲከታተሉ እና ፍሬያማ ጊዜን ማሳለፍ እንዲችሉ በማሳሰብ ንግግራቸውን አጠቃለዋል፡፡
አሁን ያለውን አመለካከት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ያስችል ዘንድ “Attitude Skills for Success at Work in Life” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሥልጠና የሰጡት የኒው አፍሪካ ኮንሰልተንሲ ፈርም መስራች፣ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና በሥራ አመራር ዘርፍ የተመሰከረላቸው አማካሪ የሆኑት አቶ አሸናፊ አበራ ሲሆኑ በሥልጠናቸውም አመለካከት በየዕለቱ በህይወታችን የምናየው እና በሚገጥሙን ነገሮች የምንፈጥረው እይታ ነው ብለዋል፡፡ በሥልጠናቸው ጨምረውም አንድ ነገር በራሱ መጥፎም ጥሩም እንዳልሆነ ነገር ግን የምንቀበልበት መንገድ መጥፎ ወይም ጥሩ እንደሚያደርገው በማንሳት ወደ አዎንታዊ አመለካካት ወይም አስተሳሰብ የመውሰድን ትልቅነት አጉልተው ማሳየት ችለዋል፡፡
ሌላው የአክስዮን ማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆኑት ወ/ሮ እንዬ ቢምር በደንበኛ አገልግሎት እና ተግባቦት ላይ ሥልጠና የሰጡ ሲሆን የተግባቦት መንገዳችን ከወላጆች እና ከተማሪዎች፣ ከድርጅቱ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም ከሌሎች ደንበኞች ጋር ምን መምሰል ይኖርበታል? ለሚነሱ ጉዳዮችስ መፍትሄ ከመስጠት አንጻር በምን መንገድ ተግባቦታችን መቃኘት ይኖርበታል? የሚለውን አጽኖት በመስጠት አሰልጥነዋል፡፡ በተጨማሪም የድርጅቱ ደንበኞች የሆኑትን ወላጆች የአገልግሎት እርካታን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን ለተሰሳታፊዎች በሚገባ አስርጸዋል፡፡
በሥልጠናው ተሳታፊ ከሆኑት መካከል የወይራ ቅድመ መደበኛ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት የሆኑት ወ/ሮ ማህሌት ኤፍሬም ሲገኙበት በሥልጠናው ትልቅ የህይወት ልምድ እንደተማሩ በመጥቀስ በእያንዳንዱ የሥልጠና ቆይታቸው ያላቸውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በማሰብ እና በማነጻጸር ትልቅ ትምህርት እንዳገኙበት ተናግረዋል፡፡
አቶ የአብስራ አለማየሁ የእግዚአብሔር አብ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሲሆኑ በሥልጠናው ያላቸውን አስተያየት አመለካከትን እንዴት መስራት እና መቀየር እንደምችል በደንብ ማየት የቻልኩበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በአጠቃላይ ከዚህ ሥልጠና በኋላ ወደየቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቻቸው ሲመለሱ በተመሳሳይ መልኩ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና አጋር አካላት የወሰዱትን ሥልጠና በማውረድ ድርጅቱ ያቀዳቸውን ስልታዊ እና ዓመታዊ ግቦች እንደሚያሳኩ ቃል የገቡ ሲሆን ድርጅቱም በዚሁ አግባብ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በመጨረሻም በሥልጠናው ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር የአክስዮን ማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታደሰ አሰፋ ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በ2015ዓ.ም ከደንበኞች አገልግሎት ጋር ያለንን ግንኙነት ከፍ የምናደርግበት እና ይሄንኑ በተግባር የምናሳይበት እንዲሁም ቃል የምንገባበት መሆን መቻል አለበት ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ያገኛችሁትን ሥልጠና ወደ ዕቅድ በማውረድ ለመስራት ዝግጁ መሆን ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ብሎም አስተሳሰብ ላይ የሚኖራችሁን አመለካከት አጎልብታችሁ በተሻለ ተግባቦት ልትጓዙ ይገባል ሲሉ የሥልጠና ተሳታፊዎችን በማሳሰብ ሥልጠናውን ለአዘጋጀው ለአክስዮን ማኅበሩ የሰው ሃብት አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ሥልጠናው ለሁለት ቀናት ለ45 ሰዎች የተሰጠ ሲሆን አመለካከትን ወይም አስተሳሰብን ወደ ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር ያስችል ዘንድ ተጨባጭ ምሳሌዎችን በማንሳት እና መመሪያ በመስጠት የተካሄደ ነው፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ወልድያ ላይ ለሚከፈተው የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ለተቀጠሩ አዲስ ርዕሰ መምህራን፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በሥራ ላይ መኖር ስለሚገባ አመለካከት እና ሙያዊ ሥነ ምግባር፣ የአክስዮን ማኅበሩ አደረጃጀት፣ ራዕይ፣ ተልኮ እና የድርጅቱ የስራ ባህል ምን ይመስላል የሚለው ላይ ትኩረት በማድረግ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ
952 viewsedited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 18:02:43
2.6K views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:35:46 የአቡነ ጎርጎርዮስ የሰሚት ሁለተኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ዮርዳኖስ ተረጨ የፈጠረውን ድሮን ለሶስት ቀናት በቆየው በከተማ ደረጃ በተዘጋጀው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራ ውድድር ላይ ድሮኑን በዚህ መልኩ ለታዳሚያን በማሳየት አድናቆትን ማትረፍ ችሏል፡፡
839 views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:19:30
ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ምስጋና አቀረቡ
**************
በባህር ዳር አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የሚገኙ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጁ፡፡
ተማሪዎቹ መምህራኑ በእውቀት እና በሥነ-ምግባር አንጸው እዚህ ስላደረሷቸው ምስጋና ይገባቸዋል በሚል በራሳቸው ተነሳሽነት ባዘጋጁት በዚህ መርሃ ግብር ላይ ለሁሉም መምህራን ምስጋናቸውን አድርሰዋል፡፡
በመሆኑም በእለቱ በተማሪዎች በተደረገው ንግግር እናንተ በገሰጻችሁን ቁጥር ልጆች ነበርን እና ቢከፋንም ለኛ መሆኑን ተረድተን ከታች ድረስ ጀምረን እዚህ ስንማር ላደረጋችሁልን ከቃላት በላይ ለሆኑ መልካም ነገሮች በሙሉ ይህ ለናንተ ትንሽ ቢሆንም በጣም እናመሰግናለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መምህራኑ በበኩላቸው በተማሪዎቹ በተዘጋጀው የምስጋና ጊዜ ላይ እስከ አሁን እንዲህ አይነት ልምድ ገጥሞን አያውቅም በማለት እጅግ እንደተደሰቱ በመግለጽ ከዚህ የበለጠ ዋጋ ከፍለን እንድናስተምር አነሳስታችሁናል ብሎም በቀሪው ጊዜ እናንተን በተሻለ መልኩ እናግዛለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ተማሪዎቹ ለትምህርት ቤታቸው የብጹህ አቡነ ጎርጎርዮስ ምስልን በትልቁ በማድረግ የሁሉም የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ስምን ከጀርባው በማስፈር ስጦታ አበርክተዋል፡፡ ከትምህርት ቤቱ ጋር ያላቸው ቆይታ በዚህ ዓመት የሚጠናቀቅ ቢሆንም እንደ ቤተሰብ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር አብረው የሚዘልቁ ይሆናል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com/e/ በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።
1.0K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:12:08
የባህር ዳር ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ተመረቁ
********************
በአቡነ ጎርጎርዮስ ባህር ዳር ቅድመ መደበኛ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 239 ተማሪዎች የቅድመ መደበኛ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ በሙሉ ዓለም የባህል ማእከል ተመረቅዋል፡፡
የምርቃት መርሃ ግብሩ በተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክት በአማርኛ፣ በግእዝ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች በመናገር የተጀመረ ሲሆን ተጨማሪ ግጥም እና ቅኔዎች በመድረኩ በመቅረብ የዝግጅቱ ድምቀት ሆነዋል፡፡
በባህር ዳር ሁለት የቅድመ መደበኛ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ሲገኙ ወ/ሮ ሰፊነሽ ጀምበር አንዷ የቅድመ መደበኛ ርዕሰ መምህርት ሲሆኑ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር እናንተ የኢትዮጵያ ተስፋዎች የሆናችሁ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች በብዙ መልኩ የአካላዊ እድገታችሁን እና ማህበራዊ ልማታችሁን ሊያሳጉ የሚችሉ ተግባራትን አከናውናችሁ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
እንዲሁም ርዕሰ መምህርቷ እናንተ ለሀገር እና ለወላጆቻችሁ ተስፋ መሆናችሁን ተረድታችሁ በትጋት ተምራችሁ ነገ በዲግሪ እና ከዛም በላይ መመረቅ መቻል አለባችሁ ያሉ ሲሆን ወላጆችም የሚፈልጉትን መስመር ልጆቹ እንዲይዙ ከጎናቸው መቆም ይኖርባችኋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ የነበራቸውን የሶስት ዓመታት ቆይታ በማጠናቀቅ እና ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ብቁ ሆነው በመገኘት ለዚህ በመብቃታቸው እጅግ ደስተኛ ሆነዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች የቅድመ መደበኛ ትምህርታቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን እና ለቀጣዩ ምዕራፍ ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከመድረኩ ተቀብለዋል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com/e/ በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።
1.6K views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ