Get Mystery Box with random crypto!

ተአምር ግዛዉ-ምነዋ / Teamer Gizaw -Minewa አያምጣዉ ነዉ እንጂ አያድርስ የሰዉ ሰ | 🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™

ተአምር ግዛዉ-ምነዋ / Teamer Gizaw -Minewa


አያምጣዉ ነዉ እንጂ አያድርስ
የሰዉ ሰዉ ተወዶ የታል ክስ
ምነዉ ፍቅርህ ትጥቄን ሊያስፈታ
በኔዉ በጭምቷ በረታ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

በማላዉቀዉ ነገር ድንገት
ተሰብስቤ ካለሁበት
ባትነካካኝ ምን አለበት
ምነዋ ምነዋ

በማለዳዉ ፍቅር ገብቶ
ልቤን በአንተ አስደስቶ
የነገርከኝን ሰንብቶ
ምነዋ ምነዋ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

አያምጣዉ ነዉ እንጂ አያድርስ
የሰዉ ሰዉ ተወዶ የታል ክስ
ምነዉ ፍቅርህ ትጥቄን ሊያስፈታ
በኔዉ በጭምቷ በረታ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

ፅኑ ፍቅሬም ላያባራ
ምኞት ህልሜን ላትጋራ
ልቤን ባልሰጥ ላንተ አደራ
ምነዋ ምነዋ

ይቀል ይሆን በምን ብርታት
ሁለት ፀፀት ሁለት ቅጣት
አንተን ማግኘት አንተን ማጣት
ምነዋ ምነዋ

አድሮ እንደጥርስ ህመም ለሚጠዘጥዘኝ
ለዚህ ለዚህ ነዉ ወይ ያንተ ፍቅር የያዘኝ
በቅናት ላይ ቅናት እየደጋገመኝ
ስንቴ ሞቼ ነበር ሳልል አመመኝ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

@Musziqahiwote_lyrics
@Musziqahiwote_lyrics