Get Mystery Box with random crypto!

ሄዋን ገ/ወልድ – ከምኔው / Hewan G/weld – Keminew ወይ ላትናገር ወይ ላትረዳ ወዲ | 🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™

ሄዋን ገ/ወልድ – ከምኔው / Hewan G/weld – Keminew

ወይ ላትናገር ወይ ላትረዳ
ወዲ ወዲያ እያልክ ደርሶ እንደ እንግዳ
ማረግህ ሳያንስ እኔን ባለዳ

ሁሉን ካሟላው ካካልህ በላይ
ከአይኔ አልፎ ድንገት ቀያይሮ ፀባይ
ምኔው ተገኘ ፍቅርህ ልቤ ላይ

ምኔው ለምጄህ ለምጄህ አረፍኩ ወድጄህ
ምኔስ ነው ስፍስፍ ነው ስፍስፍ ያረከኝ ክንፍ

አሆሆ ባልሞቁበት ፀሀይ
እህህ ባልተጠጉት ዋርካ
አሄሄ ደርሰው ልክ እንዳንተው
እህህ ማረፍ አለ ለካ

አሆሆ አካሌን ለመውረስ
እህህ እንዲ በትካዜ
አሄሄ መች እስካስብ እንኳን
እህህ ፍቅርህ ሰጠኝ ጊዜ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነውሳ
ልበ ቢስ የሆንኩት ባንተው የተነሳ

ከምኔው ከምኔው ከምኔውደሞ
እንዳልተው ያረገኝ ናፍቆትህ አዳክሞ

[ እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ሰበብስ የት አለኝ ያላንተው

እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ወይ ከኔ አካል ጎሏል ወይ ካንተው] 2x

ምነው ለምጄ ለምጄ አረፍኩ ወድጄህ
ምኔስ ነው ስፍስፍ ነው ስፍስፍ ያረከኝ ክንፍ

አሆሆ አልሰለችሽ አለኝ
አህህ ሳስብህ መዋሉ
አሆሆ ደርሶብኝ ነው ባንተ
አሄሄ የፈራሁት ሁሉ
አሆሆ እንጃልኝ መውደድህ
አህህ ምን እንደፈለገ
አሄሄ ይመልሰኝ ጀመር
እህህ ወሰድ እያረገ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነውሳ
ልበ ቢስ የሆንኩት ባንተው የተነሳ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነው ደሞ
ብክንክን ያረገኝ ናፍቆትህ አዳክሞ

[ እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ሰበብስ የት አለኝ ያላንተው

እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ወይ ከኔ አካል ጎሏል ወይ ካንተው] 2x

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነውሳ
ልበ ቢስ የሆንኩት ባንተው የተነሳ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነው ደሞ
ብክንክን ያረገኝ ናፍቆትህ አዳክሞ

@Musziqahiwote_lyrics
@Musziqahiwote_lyrics