Get Mystery Box with random crypto!

ንጽህናውን ያልጠበቀ እና የተበላሸ በርካታ ቴምር መጋዝን ውስጥ ተከማችቶ መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖ | Muslim Students

ንጽህናውን ያልጠበቀ እና የተበላሸ በርካታ ቴምር መጋዝን ውስጥ ተከማችቶ መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
-----------------------
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት መጋቢት 21 ቀን 2015 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ታይዋን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ ውስጥ መሆኑ ተጠቁሟል፡።

ግለሰቦቹ በመኖሪያ ግቢያቸው በሚገኝ መጋዘን ውስጥ የተበላሸና በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል በርካታ ቴምር ንፅህና በጎደለው ሁኔታ አስቀምጠው ለአትራፊ ነጋዴዎች በፌስታል አሽገው ከሸጡላቸው በኋላ ቴምሩ የተበላሸ መሆኑን የተገነዘቡት ገዢዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ሊያዙ ችለዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የእፎይታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከፍ/ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማወጣት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ግቢ በሚገኘው መጋዘን ውስጥ ባደረገው ፍተሻ መጥፎ ጠረን ያለው እና የተበላሸ በርካታ ቴምር ተከማችቶ መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

የወረዳ 10 አስተዳደር የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሃብቱ መካ በበኩላቸው÷ በቁጥጥር ስር የዋለው ቴምር ወደ ህብረተሰቡ ቢሰራጭ በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ጊዜና ወቅትን እየጠበቁ ሕገወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ነጋዴዎችም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦች ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ ተገንዝበው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የኛ ነገር በጣም ይገርማልኮ ....
አቦ ፖሊስ ከማህበረሰቡ ላይ ዋጋ ለመጨመር የደበቁትንም ባለሀብቶች ለህግ አቅርብልን እባክህ....እ

http://t.menuredinal_arebi