Get Mystery Box with random crypto!

➾➾ሱሁርን መመገብ፣የሱሁር ማብቂያው መቼ ነው? | ሱሁር ብሉ :የሱሁር (የሌሊት ምግብ)፡- | Muslim Students

➾➾ሱሁርን መመገብ፣የሱሁር ማብቂያው መቼ ነው?

| ሱሁር ብሉ

:የሱሁር (የሌሊት ምግብ)፡- ሱሁር መብላት የዚህችን ኡማ የፆም ሥርዓት ካለፉት ህዝቦች የሚለይ ሲሆን በውስጡ ብዙ ኸይር ነገር ይዟል ፤ ይህንንም ነቢያችን
(ሦለላሁ አለይህ ወሰለም) እንዲህ በማለት ገልፀውልናል፡-
❝ በኛና በመጽሐፍት ባልተቤቶች ፆም መካከል ያለው ልዩነት #ሱሁር መብላት ነው ❞
[ ሙስሊም ዘግበውታል ]

:በሌላ ቡኻሪና ሙስሊም በተስማሙበት ሐዲስ ነቢያችን (ሦለላሁ አለይህ ወሰለም)
:ﺗﺴﺤﺮﻭﺍ ﻓﺈﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﺴﺤﻮﺭ ﺑﺮﻛﺔ
:ሱሁር ብሉ፤ ስሁር መብላት በረካ አለውና” ሲሉ ተናግረዋል
[ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል]

የሱሁር ማብቂያው መቼ ነው?
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወስለም) እና ዘይድ ኢብን ሳቢት (ረዲላሁ ዐንሀ) ሱሁር ከበሉ በኋላ ለሱብሂ ተነሱ። ዘይድም ነቢዩን (ስለላሁ አለይሂ ወስለም) «በሱሁርና በሱብሂ ሰላት መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት ምን ያህል ነው?» በማለት ጠየቃቸው። ነቢዩም (ሰለላሁ አለይሂ ወስለም) «አምሳ የቁርኣን አያዎችን የሚያስቀራ ያህል ነው።» በማለት መለሱለት።
(ቡኻሪይ፥ 1921)
50 የቁርኣን አንቀፆችን ለመቅራት ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል? ለሚለው ዑለማዎች ከ15-20 ደቂቃ በቂ ነው ብለው ያስቀምጡታል። በዚህ ምክንያት ከሱብሂ ሰላት 20 ደቂቃ በፊት ሱሁርን ማቆም ተመራጭ ሆኖ ይቀርባል።
አዒሻ (ረዲላሁ ዐንሀ) እንዳወሳችው ደግሞ በነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወስለም) ጊዜ ቢላል የሱብሂ የመጀመሪያው ኢብን ዑሙ-ሙክቱም ደግሞ ሁለተኛውን አዛን አድራጊዎች ነበሩ። እናም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወስለም) «የቢላል አዛን ከሱሁር እንዳያግዳችሁ። ኢብን ዑሙ-ሙክቱም ሁለተኛውን እስኪያደርግ ድረስ ብሉም ጠጡም።» ብለዋል።
(ቡኻሪይ፥ 1919)
@Muslimstudentsgroup