Get Mystery Box with random crypto!

ከመጋቢት 30 ጀምሮ ለሚኒባሶች የሚደረገው የነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚቋረጥ ተገለጸ ከዚህ ቀ | Muktarovich Ousmanova

ከመጋቢት 30 ጀምሮ ለሚኒባሶች የሚደረገው የነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚቋረጥ ተገለጸ

ከዚህ ቀደም የነዳጅ ድጎማ ሲደረግላቸው የነበሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ድጎማው እንደሚቋረጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።

መንግሥት ለረጅም ጊዜ ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ መጠን የለው ድጎማን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ይህንን ለማስቀረት በሂደት የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ባወጣው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

ቀስ በቀስም መንግስት በነዳጅ ምርት ላይ የሚያደርገዉ ድጎማ የማቋረጥ እቅድ እንዳለዉ ይታወቃል፡፡

በሚኒባስ ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረገዉ መንግስት ድጎማን የማስቀረቱ አንዱ አቅድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ሆኖም የድጎማ ስርአቱን የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ማህበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሰልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሄኖስ ወርቁ ከዚህ ቀደም 170ሺ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርአት ውጪ መደረጋቸዉን ተናግረዋል።

ተሽከርካሪዎቹ ነዳጅ ድጎማን በስርዓት ባለመጠቀማቸው ከድጎማው ውጪ እንዲደረጉ ምክንያት መሆኑ አመላክተዋል።

ከፊታችን መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጅምሮ በነዳጅ ድጎማው ስርአት የሀገር አቋራጭና የከተማ አውቶቢስ ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀው እነዚህም ተሽከርካሪዎችን እስከሚቀጥሉት 5 አመታት ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡


የመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ነው