Get Mystery Box with random crypto!

በሞጆ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የአባትና የልጅ ህይወት አለፈ በሞጆ ከተማ አስተዳደር ሉቦ መ | Muktarovich Ousmanova

በሞጆ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የአባትና የልጅ ህይወት አለፈ

በሞጆ ከተማ አስተዳደር ሉቦ መጋላ በተሰኘዉ አካባቢ በትናንትናው እለት ከቀኑ 6ሰዓት ገደማ በተከሰተ የእሳት አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።
የሞጆ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንፔክተር ነጋሽ ለገሰ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በባጃጅ አሽከርካሪነት ስራ ላይ የተሰማራዉ አባት በቤቱ ዉስጥም ቤንዚን ይሸጥ ነበር ብለዉናል።
ከስራ ገብቶ በእረፍት ላይ የነበረዉ አባት አዲሱ ቢራ የ 37 አመት ጎልማሳ ሲሆን ልጅ አብርሃም አዲሱ የ3 አመት ህጻን ነበር። ለአደጋዉ መንስኤ የሆነዉ ሁለት ጄሪካን ቤንዚን በቤት ዉስጥ እንዳለ እናት ምግብ ለማብሰል ለሞከረችበት ወቅት እሳቱ መነሳቱን ነግረውናል።
አደጋዉ ካጋጠመ በኋላ የሶስት አመት ልጁን ለማዳን ወደ እሳት ዉስጥ ገብቷል የተባለዉ አባት እርሱም ሆነ ልጁ ከፍተኛ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዉ በአዳማ ሃይለማርያም ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው በትናንትናው እለት ህወታቸዉ እንዳለፈ ማለፉን የሞጆ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንፔክተር ነጋሽ ለገሰ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በአደጋዉ እናት በሰዉነቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል የተባለ ሲሆን በህክምና ክትትል ላይ ትገኛለች ሲል ብስራት ሬዲዮ ነው የዘገበው።