Get Mystery Box with random crypto!

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማስተማሪያ የግል ት/ቤቶች! '''''''''''''''''''''''''''''''' | Muktarovich Ousmanova

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማስተማሪያ የግል ት/ቤቶች!
''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
የግል ት/ቤቶች ከዘጠና ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት ትውልድ በዕውቀት ከማነፅ ይልቅ ቢዝነስ እየሰሩ እንደሆነ በ2014 ዓ.ም በታየው የ12ተኛ ክፍል ውጤት በቂ ማስረጃ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የግል ት/ቤቶች ስህተታቸውን ከማስተካከል ይልቅ ለሚቀጥለው ዓመት የተማሪዎች ክፍያ በእጥፍ እንደሚጨምሩ ከአሁኑ ወላጅ ሰብስበው እየነገሩ ነው። ነገር ግን ወላጅ ዛሬም ያልገባው ነገር ልጆቻቸው እንግሊዘኛ በመናገራቸው ያወቁ እየመሰላቸው መሸወዳቸው ነው።
የግል ት/ቤቶችም ተማሪዎችን እንግሊዘኛን አቀላጥፈው እንዲናገሩ የሚተጉትን ያህል ለዕውቀት ቦታ አይሰጡም። ቢዝነሱ ተማሪዎች እንግሊዘኛ ማሳወቅ እንደሆነ በደንብ ገብቷቸዋል። ወላጅም በዚህ እየተሸወደ ገንዘቡን ለ15 ዓመት ሲገፈገፍ ይኖራል። በመጨረሻ ልጁ ለግል ኮሌጅ የሚያበቃ ውጤት ሳያመጣ ሲቀር ህመሙ ምን ያህል እንደሆነ መግለፅ ይከብዳል።