Get Mystery Box with random crypto!

የአሮሚያ ክልል ለትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ እስከ 1 ቢልየን ብር አስተዋፅዖ ያደርጋል ተባለ ሚ | Muktarovich Ousmanova

የአሮሚያ ክልል ለትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ እስከ 1 ቢልየን ብር አስተዋፅዖ ያደርጋል ተባለ

ሚያዝያ 19፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጦርነት ሳቢያ የወደሙ የትግራይ ክልል መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት የሚውል እስከ 1 ቢልየን ብር የሚደርስ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ገለፁ።

የክልል ርዕሳነ መስተዳድራን በትግራይ ክልል ተገኝተው በጦርነቱ ሳቢያ የደረሱ ውድመቶችን በመመልከት ላይ እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቭዥን ዘገባ ያመላክታል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ "የኦሮሚያ ክልል በቅርብ ጊዜ ውስጥ 30 ትራክተሮች እንዲሁም አንድ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት ገንብቶ" ለትግራይ ክልል ህዝብ እና መንግስት ያስረክባል ብለዋል።