Get Mystery Box with random crypto!

መስከረም አበራ ለሶስተኛ ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች “ኢትዮ ንቃት” የተሰኘው የዩ-ቲዩብ መ | Muktarovich Ousmanova

መስከረም አበራ ለሶስተኛ ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች

“ኢትዮ ንቃት” የተሰኘው የዩ-ቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መስከረም አበራ፤ ዛሬ እሁድ ሚያዝያ 1 አመሻሽ ላይ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏን ባለቤቷ አቶ ፍጹም ገብረ ሚካኤል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። መስከረም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለእስር ስትዳረግ የዛሬው ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

በራሷም ሆነ በሌሎች መገናኛ ብዙኃን በምታቀርባቸው የፖለቲካ ትንታኔዎች ይበልጥ የምትታወቀው መስከረም፤ በአዲስ አበባ ጎሮ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ በቁጥጥር ስር የዋለችው 10 ገደማ በሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት መሆኑን አቶ ፍጹም ገልጸዋል። መስከረም በቁጥጥር ስር ከመዋሏ በፊት፤ በመኖሪያ ቤታቸው 50 ደቂቃዎች ገደማ የወሰደ “ብርበራ” መደረጉን ባለቤቷ ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)