Get Mystery Box with random crypto!

የራያ አላማጣ እና ባላ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ | Muktarovich Ousmanova

የራያ አላማጣ እና ባላ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ

"አማራ ነን እንጅ አማራ እንሁን አላልንም፤ በጦርነቱ ወቅት በማንነታቸው ምክንያት ታፍነው የተወሰዱ ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ይፈቱ፤ ማንነት እውነት እንጅ ፍላጎት አይደለም" የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን በማሰማት ነው የአላማጣ፣ ራያ አላማጣ እና ራያ ባላ ነዋሪዎች የቆየ የአማራ ማንነት ጥያቄያቸው እንዲመለሥ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱት።

የፌዴራል መንግሥት በተደጋጋሚ ለጠየቁት የአማራ ማንነት ጥያቄ ሕጋዊ እውቅና እንዲሠጥ በሰላማዊ ሰልፉ ጠይቀዋል።

በማንነታችን ይደርስብን ከነበረው ግፍ ተላቀን የነጻነት አየር እንድንተነፍስ ላደረገን የጸጥታ ኀይል ምስጋና እናቀርባለን ያሉት ነዋሪዎቹ መንግሥት ለቆየ የማንነት ጥያቄያችን ሕጋዊ ምላሽ እንዲሰጠን አሁንም በአጽኖት እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
በባለ ዓለምየ (አሚኮ)