Get Mystery Box with random crypto!

ባጃጆች እንዳይሰሩ መታገዳቸው በርካታ ችግሮችን እንዳስከተለ ተነገረ =======#======= የ | Muktarovich Ousmanova

ባጃጆች እንዳይሰሩ መታገዳቸው በርካታ ችግሮችን እንዳስከተለ ተነገረ
=======#=======

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በድንገት በከተማዋ ውስጥ የባጃጅ ትራንስፖርትን ላልተወሰነ ጊዜ በማገዱ ምክንያት ችግሮች ማጋጠማቸውን ለአዲስ ማለዳ ቃላቸውን የሰጡ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል፡፡

የባጃጅ ትራንስፖርት መታገዱን ተከትሎ አዲስ ማለዳ ቅኝት ባደረገችባቸው ባጃጆች ይንቀሳቀሱባቸው በነበሩ የጉዞ መስመሮች የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር መኖሩን ተመልክታለች፡፡

በዚህም የተጓዦች ረዥም ሰልፎች የተስተዋሉ ሲሆን፣ የትራንስፖርት ፍላጎቱን ለማሟላት በጋማ እንስሳት የሚንቀሳቀሱ ጋሪዎች ጥቅም ላይ የዋሉባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ተስተውሏል፡፡

የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አስተያየቱን ለአዲስ ማለዳ የሠጠ ወጣት፣ በከተማ አስተዳደሩ በድንገት የተወሰነው እግድ በሕይወቱ ላይ ስጋት እንደፈጠረበት ተናግሯል፡፡ 5 የቤተሰብ አባላቱን በሚሰራው ሥራ እንደሚያስተዳድር የተናገረው ወጣቱ፣ የገቢ ምንጬ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብሏል፡፡ የከፋ ችግር ከፊቴ ተደቅኖ ይታየኛል የከተማ አስተዳደሩ በውሳኔው ጫና የደረሰባቸውን የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶችን ጉዳይ መመልከት አለበት ሲልም ተናግሯል፡፡

“የከተማ አስተዳደሩ አካሂዳለሁ ያለውን ጥናት ባጃጆች በዚህ መልኩ ሳይታገዱ ማካሄድ ይችል ነበር።” ያሉ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ደግሞ፣ ከከተማዋ የትራንስፖርት ችግር አንጻር ውሳኔው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው ብለዋል፡፡

አሰጣጥ ላይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩ በርካቶችን አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ መ
Via
addismaleda