Get Mystery Box with random crypto!

የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ስንት ጊዜ ነው የዋጋ ተመን እየወጣለት በገዥዎች ላይ አሉታዊ ተጽኖ የሚያደርሰ | Muktarovich Ousmanova

የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ስንት ጊዜ ነው የዋጋ ተመን እየወጣለት በገዥዎች ላይ አሉታዊ ተጽኖ የሚያደርሰው

እያለ ሰው እየጠየቀ ነው።

በቅርቡ የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ተስተካክሎ ነበር፥

ብር 590 → 683 → 795 → 1,200 → ...

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ከደቂቃዎች በፊት የሚከተለውን መግለጫ ሰጥቷል

የሲሚንቶ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከ1200 ብር በታች እንዲሆን ተወሰነ
============================================

አዲስ አበባ 18/5/205(ንቀትሚ) በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች የሲሚንቶ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ 1200 ብር በታች እንዲሆን መወሰኑን የሲሚንቶ አምራቾች ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ በቅርቡ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በተደረገው የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ መሰረት የሲሚንቶ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎችና የመሸጫ ዋጋውን አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ አዱኛ በቀለ እንደገለጹት የሲሚንቶ ግብይትና ስርጭትን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ቁጥር 940/2015 ተግባራዊ በመደረጉ ሲስተዋል የነበረውን የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ ንረት ማስታገስ የተቻለ ሲሆን ሲሚንቶ አዲስ በተተመነው የመሸጫ ዋጋ ከቀጣይ ሣምንት ጀምሮ ገበያ ላይ ይውላል፡፡

በመመሪያው መነሻነት አዲስ በተተመነው ዋጋ መሰረት ሁሉም የሲሚንቶ አይነቶች በኩንታል ከ1 ሺ 200 ብር በታች በሆነ ዋጋ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች ለገበያ ይቀርባል፡፡

ለዚህ መመሪያ ተግባራዊነትም አምራቾች፣ ቸርቻሪዎች፣ ሸማቾችና ተቆጣጣሪ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡም ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡