Get Mystery Box with random crypto!

ዝርዝር ዘገባ፦ ተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር | Muktarovich Ousmanova

ዝርዝር ዘገባ፦ ተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተፈቀደላቸው

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ የወሰነው በሁለት ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው ምክንያት ለፖሊስ በተሰጠው የምርምራ ጊዜ “በቂ ስራ ተሰርቷል ማለት ስለማይቻል” መሆኑን ችሎቱ አስታውቋል። ሁለተኛው ምክንያት ጋዜጠኛ ተመስገን የተጠረጠረበት “በመገናኛ ብዙሃን ሁከት እና ብጥብጥ የማነሳሳት ወንጀል” ባለፈው ዓመት በጸደቀው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ የሚታይ መሆኑ ነው።

በችሎቱ የተጠቀሰው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ “በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል፤ በወንጀል ስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዐቃቤ ህግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ አለበት” ሲል ይደነግጋል። ጋዜጠኛ ተመስገን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለበት ግንቦት 18 ጀምሮ ለ12 ቀናት በእስር ቆይቷል።

በዛሬው የችሎት ውሎ ከተመስገን በመቀጠል ጉዳዩ የታየለት ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ነው። ከ18 ቀናት በፊት በፖሊስ የተያዘው ሰለሞን ሹምዬ እንደ ተመስገን ደሳለኝ ሁሉ የተጠረጠረው ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል ነው።