Get Mystery Box with random crypto!

አደብ የማጣት ጉዳት ‹‹ለአንድ ግለሰብ አደቡ የደስታውና የስኬቱ መሠረት ሲሆን፤ አደበ ቢስነቱ ደግ | ABX

አደብ የማጣት ጉዳት
‹‹ለአንድ ግለሰብ አደቡ የደስታውና የስኬቱ መሠረት ሲሆን፤ አደበ ቢስነቱ ደግሞ የደስታ-ቢስነቱና የስቃዩ ምንጭ ነው፡፡ የዚህችንም ሆነ የሚቀጥለውን ዓለም መልካም ነገሮች በማምጣት በኩል ከአደብ ጋር የሚስተካከል ነገር እንደሌለ ሁሉ፣ በማሳጣት በኩልም እንዲሁ አደበ-ቢስነትን የሚያህል የለም፡፡ የአደብን ምንነት እስቲ አስተውል! ዋሻ ውስጥ እንዳሉ ቋጥኙ ተንከባሎ በተዘጋባቸው ጊዜ፣ ያ ሰው ከወላጆቹ ፊት ያሳያት አደብ ባለቤቱን እንዴት ነፃ እንዳወጣቸው! በሌላ በኩል ደግሞ ሰላት ይበልጥብኛል ብሎ እናቱን ያሳዘነውን ሰው ሰዎች የማምለኪያ ቦታውን እንዲያፈርሱበት፣ እንዲደበድቡትና በብልግና እንዲከሱት በማድረግ እንዴት ፈተና ላይ እንደጣላቸው ልብ በል!?››
 
ምንጭ - የአደብ አስፈላጊነት መጽሐፍ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃህፍት መደብር
 
https://t.me/NejashiPP


https://bit.ly/3r4948i