Get Mystery Box with random crypto!

፨ በዐይናችን ላላየናቸው ግና በልባችን ላኖርናቸው ሁሉ ሰባሐል ኸይር። ፨ ዝምታችን እንደ ንግግራች | ABX

፨ በዐይናችን ላላየናቸው ግና በልባችን ላኖርናቸው ሁሉ ሰባሐል ኸይር።
፨ ዝምታችን እንደ ንግግራችን ለሚገባቸው ሁሉ ሰባሐል ኸይር።
፨ በዱዓ ለሚያስታዉሱን፣ በመልካም ለሚያወሱን፣ በበጎም ለሚጠረጥሩን ሁሉ ሰባሐል ኸይር።
፨ ከዐይናችን ቢርቁም ከልባችን ላልራቁት ሁሉ ሰባሐል ኸይር።
፨ ለነዚያ ለአላህ ብቻ ብለው ለወደዱን እና ለወደድናቸው ሁሉ ሰባሐል ኸይር።
፨ ዛሬ ምድር ላይ ብናጣቸው ነገ በአኺራ ልናያቸው ለምንጓጓቸው ሁሉ ሰባሐል ኸይር።

ሰባሐል ኸይር ቅን ለሆኑት ወዳጆቻችን ሁሉ።

ሕይወት እንደ ፀሐይ ሁሉ ናት። ትወጣለች ትገባለች። የክረምት ፀሐይ ከዳመናው ጋር እንደምትታገለው ሁሉ እኛም እስትንፋሳችን እስካለች ድረስ ዱንያን እንታገላታለን።

ሰባሐል ኸይር!

http://t.me/MuhammedSeidABX