Get Mystery Box with random crypto!

ትናናሽ ኃጢአቶች ወደ ትላልቆቹ የሚያድጉበት ምክንያቶች ምንጭ ፣ 'ወደ አላህ ሽሹ' መጽሐፍ 1- | ABX

ትናናሽ ኃጢአቶች ወደ ትላልቆቹ የሚያድጉበት ምክንያቶች
ምንጭ ፣ 'ወደ አላህ ሽሹ' መጽሐፍ

1-      በኃጢአት ላይ መዘውተር (ሙጭጭ ማለት) ፡-
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)  “ ከመዘውተር ጋር ትንሽ የሚባል ኃጢአት የለም። ከተውበት (ንስሃ) ጋር ደግሞ ትልቅ ኃጢአት የለም።”
2-      ኃጢአትን አሳንሶ መመልከት፡-  
ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “አማኝ ሰው ሃጢአቱን ልክ በራሱ ላይ ሊወድቅ እንደሚያንዣብብ ተራራ አድርጎ ይመለከተዋል። ዝንጉ (ሙናፊቅ) ሰው ግን ኃጢአቱን እጁን ቢያወናጭፍ ሊያባርራት እንደሚችል ዝንብ ነው የሚያየው።”(ቡኻሪና ሙስሊም)
 
አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡- “እናንተ እንደ ፀጉር አቅልላችሁ የምትመለከቱትን ኃጢአት በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ ከአውዳሚ ወንጀል እንቆጥረው ነበር።”        (ቡኻሪ ዘግበውታል)
 
ቢላል ኢብን ሰዕድ (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ይላል፡- “የኃጢአትህን ትንሽ መሆን አትመልከት የምታምጸውን ጌታ ታላቅነት ተመልከት።”
3-      በኃጢአት መደሰት፡-
አንድ ሰው “የእገሌን ክብር እንዴት እንዳዋረድኩትና ሃፍረት እስኪይዘው ድረስ ኃጢአቱን እየዘረዘርኩ እንዳሸማቀቅኩት አላየህምን? “ በማለት ሊናገር ይችላል። አንዱ ነጋዴ ደግሞ ለጓደኛው “ያንን ሰው እንዴት እንዳታለልኩትና እንደተጫወትኩበት አልሰማህምን?” በማለት ወንጀሉን ገድል አድርጎ ሊያወራ ይችላል። እነዚህን የመሠሉ አባባሎች ትንሹን ኃጢአት ወደ ትልቅ የሚቀይሩ ምሣሌዎች ናቸው።
4-     የአላህን ነውር የመሸፈን ፀጋ ችላ ማለት ፡-
 አላህ የአንድን ባሪያውን ኃጢአት በመሰተርና በቅጣቱ ባለመቸኮሉ መዘናጋት ታናናሽ ኃጢአቶችን ወደ ታላቅ ይቀይራቸዋል።
5-     የፈጸሙትን ኃጢአት በሌሎች ሰዎች ፊት ማውሳት፡-
አቡሁረይራ (ረ.ዐ.) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡- “ከኡመቶቼ የፈጸሙትን ኃጢአት ይፋ የሚያደርጉ ሲቀሩ ሁሉም ምህረት ያገኛሉ። ሰውዬው በሌሊት የፈጸመውን ኃጢአት አላህ የሰተረው ሆኖ እያለ ሲነጋ “እገሌ ሆይ! እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ትናንት ፈጸምኩ” በማለት ያወራል።”
6-    ኃጢአት የሚፈጽመው ሰው ሰዎች የሚመሩበት የዕውቀት ባለቤት ከሆነና የፈጸመው ኃጢአት ከታወቀ ወደ ታላቅ ኃጢአት ከፍ ይልበታል።


 https://t.me/NejashiPP